"ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፤ በህብረት እንታገል!"

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በአለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ ጊዜ በሐገራችን ደግሞ ለ19ኛ ጊዜ "ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፤ በህብረት እንታገል!"! – Uniting the World against Corruption” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘው አለም አቀፍ የጸረ ሙስና ንቅናቄ ቀን በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) በተለያዩ መርሃ ግብሮች ተከበረ፡፡

በተቋም ደረጃ በተከበረው አለም አቀፍ የጸረ ሙስና ንቅናቄ ቀን ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ እንዳሉት “ሙስና” ዘርፈ ብዙ መገለጫ ያለው፤ የትውልድን ተስፋ የሚያጨልም በአጠቃላይም የሃገርን ሕልውና አደጋ ውስጥ የሚጥል ነቀርሳ በመሆኑ ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል በጋራ በመሆን ሙስናን ሊታገል ይገባል ብለዋል፡፡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እንደ አንድ የጸጥታና ደህንነት ተቋም ከሙስናና ብልሹ አሰራር የጸዳ ተቋም ከመገንባት ባሻገር ሐገር አቀፍ የሙስና ትግሉን ለመደገፍ የሚያስችሉ የተለያዩ ሥራዎችን በመስራት አበርክቶ የሚያደርግ መሆኑንን ጠቁመው፤ ለአብነትም በሐገር አቀፍ ደረጃ የሙስና ጥቆማዎችን ለመቀበል የሚያስችል ሲስተም በማበልጸግ ለፌዴራል የሥነ ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ማስረከቡ የሚታወስ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘው እንደገለጹት በሐገር አቀፍ ደረጃ የተቋቋመው “ብሄራዊ የጸረ ሙስና አስተባባሪ ኮሚቴ” በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ የተለያዩ የሙስና ወንጀሎችን በመከታተል ለሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ የማድረግና የሐገርና የሕዝብ ሃብት እንዲመለስ ማድረግ መቻሉንም ገልጸዋል፡፡

የኢመደአ የሥነ ምግባርና ጸረ ሙስና መከታተያ ዲቪዥን ሃላፊ ኮ/ል ጸሃዬ ግደይ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት በተቋም የሥነ ምግባርና ጸረ ሙስና የኝዛቤ መፍጠሪያ መድረኮችን ቀጣይነት ባለው መልኩ በማዘጋጀት እንዲሁም የአስተዳደሩን አባላትና አመራሮች የሃብት ምዝገባ በየወቅቱ በማከናወን ከሙስና የጸዳና በአርአያነት የሚጠቀስ ተቋም የመገንባት ሥራ እየተሰራ እንደሆነና በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች