"ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" ስኬት የሳይበር ደህንነትን ማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንዳለዉ ተገለጸ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

"የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" ስትራቴጂ ስኬት የሳይበር ደህንነትን ማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንዳለዉ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር / ትዕግስት ሃሚድ በዲጂታል ኢትዮጵያ የግማሽ ዘመን ግምገማ ላይ ገለጹ።

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 እውን ለማድረግ በሃገር አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ተቋማት ሃላፊነቶችን ወስደዉ እያከናወኑ መሆኑን የጠቆሙት ሃላፊዋ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርም ሀገራዊ የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን በማረጋገጥና የሳይበር ምህዳሩን ሉዓላዊነት በማስጠበቅ የራሱን ሚና እየተወጣ እንደሚገኝ / ትዕግስት በመድረኩ ተናግረዋል።

ያለ ሳይበር ደህንነት የዲጂታል ኢትዮጵያን 2025 ዕዉን ማድረግ አስቸጋሪ መሆኑን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሯ እቅዱን እዉን ለማድረግ በዲጂታል ምህዳሩ ላይ የነቃና ለሳይበር ደህንነት ትኩረት የሚሰጥ ማህበረሰብ መፍጠር እንደሚገባም አንስተዋል።

የዲጂታል ምህዳሩን የመጠቀም ፍላጎት እያደገ ሲሄድ በተቋማትና በግለሰቦች ላይ የሚሰነዘሩ የሳይበር ጥቃቶች እንደሚጨምር የገለጹት / ትዕግስት ከዕድገቱ ጋር አብሮ የሚሄድ የጥንቃቄና የመከላከል ስራ መስራት ወሳኝ መሆኑን በመድረኩ ጠቁመዋል።