ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኙ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በዛሬው ዕለት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ጎብኝተዋል፡፡

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና መስሪያ ቤት ተገኝተው የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅና እንደ ሀገር የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን ለማረጋገጥ በአስተዳደሩ እየተሠሩ የሚገኙ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችንና በመልማት ላይ ያሉ ምርትና አገልግሎቶችን ተዟዙረው ጎብኝተዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ በኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ትዕግስት ሃሚድ አማካኝነት በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በመገንባት ላይ የሚገኘውን ይፋዊ ቁልፍ መሠረተ ልማት ጨምሮ የዳታ ማዕከል፣ የተቀናጀ የክፍያ ሥርዓት(ደራሽ) ኢትዮ ሰርትን፣ ዲጂታል የመሬት አስተዳደር ሥርዓት፣ የሳይበር ታለንት ልማት ማዕከልን፣ ደህንነተታቸው የተጠበቁ የመገናኛና ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ምርቶችና አገልግሎቶችን ተዟዙረዉ ተመልክተዋል፡፡

በጉብኝቱ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በሰው ኃይል፣ በአሠራር ሥርዓት፣ በቴክኖሎጂ፤ በአጠቃላይ በከፍተኛ ደረጃ ዕድገት እያስመዘገበና በሁለንተናዊ የለውጥ ጎዳና ዉስጥ መሆኑን መመልከታቸውንና ባዩት ነገርም መደሰታቸውን ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ተናገረዋል፡፡

ከለውጡ ጊዜ ጀምሮ አስተዳደሩ በርካታ የማሻሻያና የሪፎርም ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን እንደሚያውቁና በሪፎርም ሥራው ከፍተኛ ለውጥ እየተመዘገበበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም አስተዳደሩ እንደ ሀገር የተሰጠውን የሃገሪቱን የኢንፎርሜሽን እና የኢንፎርሜሽን መሠረተ ልማቶች ከጥቃት የመጠበቅና የኢንፎርሜሽን የበላይነትን የማረጋገጥ ተልዕኮ ለመወጣት በሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝና ተልዕኮውን በላቀ ደረጃ ለመፈጸም የሚያስችሉ አዳዲስ ሥራዎችን እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይህ የተቋሙ ቁመና መጀመር ብቻ ሳይሆን መፈጸም የሚችልበት አቅም መፍጠሩን  እንደተመለከቱ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል፡፡ 

አስተዳደሩ የተሰማራበት ዘርፍ በከፍተኛ ደረጃ በዕድገት ላይ ያለና እንደሃገር ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ትኩረት እየተሰጠው የሚገኝ እንደመሆኑ መጠን በቀጣይም ተቋሙ ለሚያከናውናቸው ሥራዎች ለሚገጥሙት ተግዳሮቶች የመንግሥት ትኩረትና የቅርብ ድጋፍ እንደማይለየው አረጋግጠዋል፡፡

ከጉብኝቱ በኋላ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር / ትዕግስት ሃሚድ በበኩላቸዉ ኢመደአ ባለፉት 6 የለዉጥ አመታት ራሱን ለማላቅ የሰራቸዉን መጠነ ሰፊ ስራዎች፣ ያለፈባቸዉን ዉጣ ዉረዶች እንዲሁም ተቋሙ ባስመዘገባቸዉ ስኬቶች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል።

በገለጻቸዉም ኢመደአ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወነ ያለዉን የዲጂታል ሽግግር የሚደግፉ የሳይበር ደህንነት መፍትሄዎች የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ስላሉ ተግባራት እንዲሁም የዲጂታል ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ እየተደረገ ስላለ ተጋድሎ እንዲሁም ተቋሙ በቀጣይ በትኩረት ሊሰራባቸዉ ባቀዳቸዉ ወሳኝ ጉዳዮች ዙሪያ ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርበዋል።

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች