የሳይበር ደህንነት እና የወጣቶች ሚና በሚል ርዕስ የውይይት መድረክ ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሃገራዊ የሳይበር ደህንነትን በማረጋገጥ ረገድ የታዳጊ ወጣቶች ሚና ወሳኝ እንደሆነ ተገለጸ፡፡ በ4ኛው ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የሶስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ ተማሪዎች እንዲሁም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ከሌሎች የግል ዩኒቨርሲቲዎች ለተውጣጡ ተማሪዎች “የሳይበር ደህንነት እና የወጣቶች ሚና” በሚል ርዕስ የውይይት መድረክ በዛሬው እለት ተካሂዷል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ታዳጊ ወጣቶች ማህበራዊ ሚዲያን አዎንታዊ በሆነ መልኩ በመጠቀም ለሃገራዊ የሰላም ግንባታ የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ የሐገራችንን ሕልውና ከሚፈታተኑ ጉዳዮች መካከል በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቀቁ ሃሰተኛ መረጃዎች አንዱ ሲሆን፤ ከዚህ አኳያ ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያ የሚያጋሯቸውን መረጃዎች ትክክለኛነት በማጣራት መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ አያይዘው እንደገለጹት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የዜጎችን በተለይም ደግሞ የታዳጊ ወጣቶችን የሳይበር ደህንነት ንቃተ ሕሊና ለማሳደግ የተለያዩ ሥራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው፤ በቀጣይም ከትምህርት ቤቶች ጋር በመቀናጀት የታዳጊ ወጣቶችን የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ የመገንባት ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ወጣቶች በሰጡት አስተያየት እንደ ሐገር የራሳችን የሆነ የማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርም መገንባት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሐገሪቱን የሳይበር ደህንነት ለመጠበቅ እየሰራቸው ያሉ ሥራዎች፤ በተለይም ደግሞ አስተዳደሩ በራስ አቅም ያለማቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች እንደ ሐገር ትልቅ ተስፋን የሚጭሩ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ከውይይት መድረኩ ባሻገር በውይይቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ወጣቶች የአስተዳደሩን የሳይበር ታለንት ልማት እንዲሁም የዲጂታል ኤግዚቢሽን ማዕከል ጎብኝተዋል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች