17ኛው የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በተገኙበት ተከፈተ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ኢትዮጵያ ያስተናገደችው  17ኛው ዓለም አቀፉ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በተገኙበት በዛሬው እለት በይፋ ተከፍቷል፡፡

በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ባለፉት አራት አመታት በይነ መረብ በኢትዮጵያ ላይ መልካምም መጥፎም አስተዋጽኦ እንደነበረው ገልጸዋል፡፡ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ ይህንን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ኢንተርኔት በጎ ሚና እንደነበረው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በአንጻሩ ሃሰተኛና አፍራሽ መረጃዎችን በማዛመት በኩል ደግሞ አሉታዊ ሚና ነበረው ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ለጉባኤው ተሳታፊዎች እንደገለጹት ኢትዮጵያ በዲጂታላይዜሽን በኩል የሄደችበት ርቀትና ቁርጠኝነት ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ለአብነትም የ4G እና 5G ማስፋፊያ ሥራዎች፣ የዲጂታል ሥነ ምህዳር (Eco-system) ግንባታ፣ የግል ኢንቨስተሮች በቴሌኮም ዘርፍ እንዲሳተፉ የተደረገበት እና በሳይበር ደህንነት እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ የተሰሩ ሥራዎችን ጠቅሰዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ አያይዘው እንደጠቀሱት በዳታ ደህንነት፣ በኢንተርኔት ትስስር ግንባታ እና መመሪያና ፖሊሲዎች ላይ ትብብር እንደሚያስፈልግ ገልጸው ግዙፍ የሆኑ የማህበራዊ ሚዲያ ተቋማት በመረጃ ደህንነት አጠባበቅ ላይ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡

የጉባኤው ተሳታፊዎች በሳይንስ ሙዚየም የቀረቡና የኢትዮጵያን የዲጂታል 2025 ጉዞን የሚያሳዩ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን እንዲመለከቱ የጋበዙ ሲሆን፤ ጉባኤው ጠንካራ የፖሊሲ አማራጭና የተሳካ መድረክ እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡  

ከትላንት ህዳር 19 እስከ  ህዳር 23 ቀን 2015 ዓ.ም እየተካሄደ በሚገኘው 17ኛው ዓለም አቀፍ የበይነ መረብ  አስተዳደር ጉባኤ ላይ ከሶስት መቶ በላይ ሁነቶች የሚከናወኑ ሲሆን ኢትዮጵያን ለውጭው ዓለም በበጎ ጎን የሚያስተዋውቁ ልዩ ልዩ ተግባራት ይከወናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በጉባኤው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤና የተለያዩ የውጭ ሀገራት ተወካዮች ተገኝተዋል።