65 በመቶ ኢትዮጵያዊያን ዝቅተኛ የሳይበር ደህንነት ንቃተ ሕሊና ደረጃ እንዳላቸው ተገለጸ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

65 በመቶ ኢትዮጵያዊያን ዝቅተኛ የሳይበር ደህንነት ንቃተ ሕሊና ደረጃ እንዳላቸው በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) የተሰራ ሃገራዊ የሳይበር ደህንነት ንቃተ ሕሊና ደረጃ ጥናት ውጤት አመለከተ፡፡

በ4ኛው ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የሦስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ላይ “ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊና ደረጃ ጥናት ሪፖርት” ይፋ ሆኗል፡፡ በዚህም 65 በመቶ ኢትዮጵያዊያን ዝቅተኛ የሳይበር ደህንነት ንቃተ ሕሊና ደረጃ እንዳላቸው ተገልጿል፡፡

ጥናቱ በሐገር አቀፍ ደረጃ በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ወጥ በሆነ መልኩ የተሰራ የመጀመሪያ ጥናት እንደሆነም ተነግሯል፡፡

ጥናቱ እንደሚያሳየው ከ33 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን የኢንተርኔትና የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እንዳሉ አመላክቶ ከነዚህ ከተመረጡ ናሙናዎች 6106 የሚሆኑት ለጥናቱ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ከጥናቱ ተሳታፊዎች ከ77 በመቶ በላይ የሚሆኑት ከዲፕሎማ እስከ ፒ.ኤች.ዲ. ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ያላቸው እንደሆኑ የጥናቱ ስታትስቲክስ ያሳያል፡፡

ጥናቱ በዋናነት በኢትዮጵያ የሳይበር ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ዜጎች ስለ ሳይበር ደህንነት ያላቸው የእውቀት (Knowledge) ፣ የአመለካከት (Attitude) እና የአጠቃቀም (Practice) ደረጃ ምን ይመስላል በሚል ጭብጥ ላይ የሚያጠነጥን ነው፡፡

በጠቅላላው የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊና እውቀት ደረጃ ሲለካ 35 በመቶ የሚሆኑት ብቻ አውቀው የሚንቀሳቀሱ እንደሆነና 53 በመቶ የሚሆኑት ስለሳይበር ደህንነት አወንታዊ አመለካከት እንደሌላቸው የጥናት ውጤቱ አመላክቷል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅ በአጠቃቀም ዙሪያ መወሰድ ከሚገባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች በአማካይ 50 በመቶ የሚሆኑት ብቻ መልካም ልምድ እንዳላቸው ተገልጿል፡፡ በተለይም 73 በመቶ የሚሆኑት ጠንካራ የይለፍ ቃል ከመጠቀም አኳያ ችግር እንዳለባቸው ዝርዝር ውጤቱ ያሳያል፡፡

በኢትዮጵያ ይህ ከፍተኛ የሆነ የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊና ክፍተት ለሁሉም የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ዜጋ እኩል ስጋት እንደሆነ ገልጾ፤ በተለመደው የስነ-ትምህርት ስርዓት በማሳደግና በማስፋፋት ብቻ ክፍተቱን ለመዝጋት እንደማይችል ጥናቱ ይደመድማል፡፡

በመጨረሻም በፖሊሲ የታገዘ የሳይበር ደህንነት ንቃተ ህሊና ጉዳዮች ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው እና የተቋማት የእቅድና የበጀት አካል ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ይገልጻል፡፡ በተጨማሪም የግልና የሕዝብ ተቋማት፣ ልዩ ልዩ አደረጃጀቶችን እንዲሁም ሚዲያን በመጠቀም በተለያየ ደረጃ የዜጎችንና የተቋማትን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ የማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ትምህርት በመስጠት በእውቀት፣ በአመለካከትና በአጠቃቀም ዙሪያ የሚፈለጉ ባህሪያቶችን (Intended behaviors) መፍጠር እንደሚገባ የጥናቱ ምክረ ሀሳብ ያስረዳል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች