የሳይበር ታለንት የክረምት ስልጠና መርሃ-ግብር ተመራቂዎች የአዲስ ምዕራፍ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) በክረምት መርሃ ግብር በሳይበር ታለንት አሰልጥኖ ላስመረቃቸው ባለ ልዩ ተሰጦ ታዳጊዎች የአዲስ ምዕራፍ ማስጀመሪያ ፕሮግራም አካሄደ ፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ በክረምት መርሃ ግብር በሳይበር ታለንት ሰልጥነው ያስመረቃቸው ባለተሰጦ ታዳጊዎች ወደ አዲስ ምዕራፍ በመሸጋገራችሁ የእንኳን ደስ አላቹህ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ባስተላለፉት መልዕክት የመጀመሪያው የክረምት መርሃ-ግብር (ሰመር ካምፕ) የሳይበር ታለንት ተመራቂ በመሆናቹህ ሀገራችሁ ከእናንተ ብዙ ትጠብቃለች ለዚህ ስኬትም የበኩላችሁን እንድትወጡ ሲሉ አሳስበዋል ፡፡

በሰመር ካምፕ መርሃ ግብር በተናጠል በተለያዩ ዘርፎች ፈጠራዎች በመስራት አበረታች ውጤት ማስመዝገባቸውን ያስታወሱት ዋና ዳይሬክተሩ በዚህ አዲስ ምዕራፍ በየዘርፉና በዝንባሌያቸው መሰረት በቡድን ትልቅ ሀገር በቀል ፕሮጀክት ተሰጥቷቸው እንደሚሰሩ የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ ቀሪዎቹ ደግሞ በአስተዳደሩ ተቀጥረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም በዚህ አዲስ ምዕራፍ አስተዳደሩ በግንባር ቀደምትነት የታዳጊዎችን የፈጠራ ችሎታና አቅም ለሀገር ጥቅም እንዲውል ተቋማት እና የግል ባለሃብቶች ባለልዩ ተሰጥኦ ታዳጊዎችን በማገዝ የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትግስት ሃሚድ በበኩላቸው ፈተናዎች ቢኖሩም ፈተናዎችን ተቋቁማቹሁ እና ለችግሮቹ የመፍትሄ አካል የሆናቹሁ የነገ ሃገር ተረካቢ በመሆናቹሁ ልትኮሩ ይገባል ብለዋል፡፡

ባለልዩ ተስጥኦ ታዳጊዎች ዝንባሌያቸውን እንዲለዩ እና ለአዲስ ምዕራፍ እንዲደርሱ አስተዋፆ ላደረጉ አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ባለልዩ ተሰጥኦ ታዳጊዎችም የተጣለባቸውን ሀገራዊ አደራና ኃላፊነት በቁርጠኝነት ለመወጣት ቃል ገብተው አስተዳደሩ ለሰጣቸው እድል እና ላደረገላቸው እገዛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች