የጊኒ ቢሳው ፕሬዚዳንት ኡማሮ ሲሶኮ ኢምባሎ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኙ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የሚገኙት የጊኒ ቢሳው ፕሬዚዳንት ኡማሮ ሲሶኮ ኢምባሎ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ጎበኙ።

መደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ ለፕሬዝዳንቱና ለልዑካን ቡድናቸው አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን የአስተዳደሩን የዲጂታል ኤግዚቢሽን እና የሳይበር ታለንት ልማት ማዕከልን ለእንግዶቹ አስጎብኝተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ከጉብኝቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት ስለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል በማመስገን፣ ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ በተለይም በሳይበር ደህንነት እንዲሁም ሃገራዊ የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን ለማረጋገጥ እየሠራች ያለችው ተግባር አበረታች መሆኑን ተናግረዋል።

ኢመደአ በሳይበር ታለንት ልማት ማዕከል ታዳጊ ወጣቶችን መሰረት አድርጎ እያከናወነ የሚገኘው የሳይበር ታለንት ልማት ሥራ በእጅጉ የሚደነቅ መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ ጨምረው ገልጸዋል