ኢመደአ እና የኢፌዲሪ መከላከያ ዋር ኮሌጅ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎረሜሽን መረብ ደንነት አስተዳደር (ኢመደአ) እና የኢፌዲሪ መከላከያ ዋር ኮሌጅ በሳይበር ደህንነትና ተያያዥ ዘርፎች ዙሪያ ጥናትና ምርምሮችን በጋራ ለመስራት፣ በሁለቱ ተቋማት የሚገኙ የሳይበር ደህንነት እና ወታደራዊ አቅሞችንና እውቀቶችን በጋራ ለመጠቀምና ስልጠናዎችን ለመስጠት እና በተለያዩ መሰል ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

የመግባቢያ ሰነዱን የፈረሙት የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ እና የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ኮማንዳንት ብርጋዴር ጄኔራል ቡልቲ ታደሰ ናቸው፡፡

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በፊርማ ፕሮግራሙ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የሃገርን ብሔራዊ ደህንነት ለማስጠበቅ በተለያዩ ተቋማት የሚገኝን አቅም በማስተሳሰር መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸው ኢመደአ እና መከላከያ ዋር ኮሌጅም ያላቸውን እምቅ ወታደራዊና የሳይበር ደህንነት አቅም በማቀናጀት የሀገርን ደህንነት በተሻለ ሁኔታ ለማስጠበቅ የመግባቢያ ስምምነቱ ትልቅ ሚናን እንደሚጫወት ተናግረዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘው እንደገለጹት ሁለቱ ተቋማት በጋራ በመሆን ነገን ታሳቢ ያደረገ ጥናት እና ምርምር ከወዲሁ በመጀመር የወታደራዊ ሳይንስ እና ጥበብን ለማሻሻል አብሮ መስራት ወቅቱ የሚጠይቀው እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ወደፊትም የሀገሪቱን ጸጥታ እና ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት ከተሰጣቸው ተቋማት ጋር በመደመር መስራት አስፈላጊ መሆኑን አቶ ሰለሞን ጠቅሰው፤ ይህ ዛሬ የተፈረመው የትብብር ሰነድ የሀገሪቱን ህልውና በማስጠበቅ ረገድ አንድ እርምጃ ወደፊት የሚወስድ እንደሚሆን ተስፋቸውን ገልጸዋል፡፡

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ኮማንዳንት ብርጋዴር ጄነራል ቡቲ ታደሰ በበኩላቸው የጦር አካዳሚው ግንባር ቀደም የጦር ትምህርት ቤት እና የምርምር ተቋም እንደሆነ ገልጸው፣ ብቃት ያላቸው ስትራቴጂያዊ ከፍተኛ የጦር መሪዎችን፣ ሲቪል የሀገር ደህንነት አመራሮችን እና ለሀገራችን ብሎም ለቀጠናው ሰላም እና መረጋጋት ክፍተኛ አስተዋጽኦ ሊያደርጉ የሚችሉ የውጭ ሀገራት ከፍተኛ የጦር መኮንኖችን እንደሚያሰለጥን ገልጸዋል፡፡

በሳይበር ደህንነት እና አዳዲስ ቴክኖሎጂ ዙሪያ ከፍተኛ እውቀትና ልምድ ካለው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር  በጋራ መስራት መቻል የኮሌጁን አቅም ከማሳደግ ባለፈ ለብሔራዊ ደህንነት መጠበቅም አስቻይ እንደሆነ ብርጋዴር ጄነራል ቡቲ ታደሰ ተናግረዋል፡፡

በሁለቱ ተቋማት የሚገኙ ብቁ ባለሙያዎችን በጋራ በመጠቀም የእቀት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር በማድረግ ሁለቱን ተቋማት ወደተሻለ ደረጃ ሊያደርስ የሚችል የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙ ትልቅ እርምጃ እንደሆነ የገለጹት ብርጋዴር ጄነራል ቡቲ ስምምነ በዚህ ተለዋጭ እና ውስብስብ በሆነ የቴክኖሎጂ ዓለም ተባብሮ በመስራት  የሀገርን ደኅንነት በተሻለ ደረጃ ስጠበቅ እንደሚረዳ አስገንዝበዋል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች