የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ አለማቀፍ የቴሌኮሚዩኒኬሽን ሕብረት የአፍሪካ ዳይሬክተርን ተቀብለው አነጋገሩ
የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ አለማቀፍ የቴሌኮሚዩኒኬሽን ሕብረት የአፍሪካ ዳይሬክተርን ተቀብለው አነጋገሩ
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ አለማቀፍ የቴሌኮሚዩኒኬሽን ሕብረት የአፍሪካ ዳይሬክተር አነ ራቼል ኢን በቢሯቸው ተቀብለው በቀጣይ ሁለቱ ተቋማት በጋራ በሚሰሩባቸው ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አደረጉ፡፡
በውይይታቸውም የሳይበር ደህንነትን በቅንጅት ከማስጠበቅ አኳያ ከአፍሪካ የሳይበር መከላከልና ምላሽ መስጫ (Africa CERT) ጋር በጋራ በመሆን እንደሚሰሩ የገለጹ ሲሆን፤ ኢመደአ በተለያዩ አለማቀፍና አህጉር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ኮንፍረንሶችና ኤግዚቢሽኖች ላይ ያለውን ተሳትፎ ለማሳደግም በጋራ እንደሚሰሩ ተነጋግረዋል፡፡
የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ ተቋሙ በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ያለማቸውን ምርት እና አገልግሎቶችን እንዲሁም በኢትዮ ሳይበር ታለንት ልማት ማዕከል የሚገኙ ታዳጊዎች በተለያዩ የሳይበር ደህንነት ዘርፎች የሰሯቸውን ስራዎች ለአነ ራቼል ኢን ገለፃ አድርገውላቸዋል፡፡
አለማቀፍ የቴሌኮሚዩኒኬሽን ሕብረት የአፍሪካ ዳይሬክተር አነ ራቼል ኢን ከውይይቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት ኢመደአ የኢትዮጵያን የሳይበር ደህንነት በማረጋገጥ ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ እድገት ከመደገፍ አንፃር እየሰራቸው ባሉ ነገሮች እንደተደሰቱ ገልፀው በቀጣይ ሁለቱ ተቋማት ተቀናጅተው መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውጤታማ ሥራዎችን እንዲሰሩ የበኩላቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡