የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከሜታ/ፌስቡክ ድርጅት ጋር በመተባበር ለኮሚዩኒኬሽን ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ከሜታ/ፌስቡክ ድርጅት ጋር በመተባበር “የፌስቡክ ገጽ አስተዳደር እና ደህንነት” በሚል ርዕስ ከመንግስት ተቋማት ለተውጣጡ እና የየተቋሞቻቸውን የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ለሚያስተዳድሩ የኮሚዩኒኬሽን ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ ፡፡

ስልጠናው በሜታ/ፌስቡክ ተቋም በተለያየ የኃላፊነት ደረጃ ላይ በሚገኙ አሰልጣኞች የተሰጠ ሲሆን የመንግስት ተቋማት ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ዋትስአፕን እንዴት መጠቀም፣ ማስተዳደር እና ደህንነትን መጠበቅ እንደሚገባ ያመላከተ ነበር፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ዋትስአፕን የሚያስተዳድሩ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች የተቋማቸውን ማህበራዊ ገጽ ምን መምሰል እንደሚገባው፤ የይለፍ ቃሎችን እንዴት ማዘመን እንዳለባቸው፤ የማህበራዊ ሚዲያ ደህንነትን በየጊዜው በምን መልኩ ማረጋገጥ እንደሚችሉ፤ እንዲሁም ገጾቹን የማስተዳደር ኃላፊነት ለሌሎች በሚያዘዋውሩበት ወቅት መወሰድ ስላለበት ጥንቃቄ በስልጠናው ወቅት በስፋት ተዳሷል፡፡

በስልጠናው የተሳተፉ ከመንግስት ተቋማት የተውጣጡ የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የስልጠናውን አስፈላጊነትና ወቅታዊነት በመግለጽ በቀጣይም የግንኙነት መስመር በመፍጠር በየጊዜው የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመመካከር መፍታት እና ወቅታዊና ቀጣይነት ያላቸው የደህንነት መፍትሄዎችን መጋራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች