ባለፉት 9 ወራት 453 የተከለከሉ የመረጃ እና የመገናኛ ቴክኖሎጂ እቃዎች ወደ ሀገር እንዳይገቡ ፍቃድ ተከልክሏል

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

ኢንፎሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) በ2015 በጀት አመት ባለፉት 9 ወራት ባደረገው የቁጥጥር ሥራ 453 የሚሆኑ የመረጃ እናመገናኛ ቴክኖሎጂ  መሳሪያዎች ለሀገር ደህንነት ስጋት በመሆናቸው ወደ ሀገር እንዳይገቡ ፈቃድ መከልከሉን ገልጿል፡፡

በኢመደአ የመረጃና መገኛ ቴክኖሎጂ ቁጥጥር ዲቪዥን ኃላፊ አቶ እሸቱ ቡሬሳ እንደገለጹት ወደ ሀገር እንዳይገቡ ክልከላ ከተደረገባቸው የመገናኛ ቴክኖሎጂ  መሳሪያዎች መካከል አብዛኞቹ  አደገኛ የስለላ እና ቅኝት ሥራ ሊውሉ የሚችሉ መሳሪያዎች ሲሆኑ እንደ የመገናኛ ሬዲዮኖች፣ የሳተላይት ስልኮች ጂፒኤሶች እና ሌሎችም መሰል መሳሪያዎች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ እነዚህ መሳሪዎች ተቀናጀ የወንልና የሽብር ድርጊት ለመፈጸም እንዲሁም ለህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ተግባራት ሊውሉ የሚችሉ በመሆናቸው ምክንያት ወደ ሀገር እንዳይገቡ መደረጋቸውን አቶ እሸቱ ተናግረዋል፡፡

ወደ ሀገር እንዳይገቡ ክልከላ ከተደረገባቸው የመገናኛ ቴክኖሎጂ መሳሪያዎች መካከል  ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዘው ደግሞ ለቴሌኮም ማጭበርበሪያ የሚውል የሲም ሳጥን (SIM Boxes) መሆኑን አቶ እሸቱ ገልጸዋል፡፡ እነዚህ የቴሌኮም የማጭበርበሪያ መሳሪያዎች ወደ ሀገር ገብተው  አገልግሎት ላይ ቢውሉ ኖሮ ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራን በሃገር ገቢ የሚያስከትሉ ሲሆን ከዚህም ባሻገር አጭበርባሪዎቹ ገንዘቡን ለሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር፣ ለሽብር ተግባር እና ለተጨማሪ የወንጀል ድርጊት ሊጠቀሙት ይችሉ እንደነበር አቶ እሸቱ ጨምረው ገለጸዋል፡፡

የመረጃ እናመገናኛ ቴክኖሎጂ አስመጪዎች ወይም ለድርጅታቸው አስፈላጊ ሆኖ ከውጪ ማስገባት የሚፈልጉ አካላት ቅድመ -ፈቃድ አገልግሎት ቢያገኙ እቃውን ካስመጡ በኋላ ከሚደርስ ኪሳራ፣ የመጋዘን ኪራይ፣ የጊዜ ብክነትና እንግልት ሊድኑ ይችላሉ፡፡

በመሆኑም ከላይ የተዘረዘሩትን የመረጃ እናመገናኛ ቴክኖሎጂ ለማስመጣት የሚፈልግ አካል www.esw.et/esw-trd አድራሻ የሚያስመጡትን የመረጃ እናመገናኛ ቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ዝርዝር መረጃ (specifications) በመላክ የቅድመ -ፈቃድ አገልግሎት ማግኘት የሚችሉ መሆኑን አቶ እሸቱ አበራ ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊና ተጨማሪ የሳይበር ደህንነት መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.insa.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/INSA.ETHIOPIA

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/@cyberigna1003/featured

ቴሌግራም፦ https://t.me/insagovet

ትዊተር፦ https://twitter.com/INSAEthio

ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@insa.gov

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች