የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር ጋር ውይይት አደረጉ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

ዲስ አበባ፡ ሐምሌ 20/2015 ዓ/ም፡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር ፋታላህ ሲጂልማሲ ጋር አፍሪካዊ የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን ማረጋገጥ በሚቻልበት አጀንዳ ዙሪያ ውይይት አደረጉ፡፡

አፍሪካ ከእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ለመውጣት በዋናነት የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን ማረጋገጥና ከውጭ የቴክኖሎጂ ጥገኝነት መላቀቅ እንደሚገባት የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር ፋታላህ ሲጂልማሲ በውይይቱ ላይ ገልጸዋል፡፡ ለዚህም የኢትዮጵያ ተሞክሮ ለሌሎች የአፍሪካ አገራት ጥሩ ምሳሌና መነሻ ሊሆን እንደሚችልም ተናግረዋል፡፡ የኮሚሽኑ ዋና ዳይሬክተር አያይዘው እንደገለጹት በኢመደአ በነበራቸው ጉብኝት የተመለከቷቸው ሃገር በቀል የቴክኖሎጂ ምርትና አገልግሎቶች ወደ ሌሎች የአፍሪካ አገራት መስፋፋት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡ የሁሉንም የአፍሪካ አገራት አቅምና ተሞክሮ በመደመር አፍሪካዊ የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን ማረጋገጥ እንደሚገባም ፋታላህ ሲጂልማሲ ተናግረዋል፡፡

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በበኩላቸው ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር ፋታላህ ሲጂልማሲ ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸው፤ ኢመደአ እንደ ተቋም በቴክኖሎጂ ባለቤትነት እና በዲጂታላይዜሽን ዙሪያ ያካበተውን አቅም፣ ልምድና እውቀት ለሌሎች የአፍሪካ አገራት አቻ ተቋማት ለማካፈል ዝግጁ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ አያይዘውም አፍሪካዊ ማንነትን የተላበሰ የዲጂታል ኢኮኖሚ በመገንባት እና የቴክኖሎጂ ባለቤነትን በማረጋገጥ የአፍሪካን ብልጽግና ማረጋገጥ እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ፋታላህ ሲጂልማሲ ጋር ካደረጉት ውይይት በተጨማሪ የአስተዳደሩን የዲጂታል ኤግዚቢሽን ማዕከል እና የታለንት ልማት ማዕከል አስጎብኝተዋቸዋል፡፡

ወቅታዊና ተጨማሪ የሳይበር ደህንነት መረጃዎችን ለማግኘት፡-

 

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/INSA.ETHIOPIA

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/@cyberigna1003/featured

ቴሌግራም፦ https://t.me/insagovet

ትዊተር፦ https://twitter.com/INSAEthio

ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@insa.gov