በ2015 በጀት አመት 583 የመረጃ እና የመገናኛ ቴክኖሎጂ እቃዎች ወደ ሃገር እንዳይገቡ ተከልክሏል

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]
አዲስ አበባ፡ ሐምሌ 21/2015 ዓ/ም፡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) በ2015 በጀት ዓመት ወደ ሃገር በሚገቡና ከሃገር በሚወጡ የመረጃ እና መገናኛ ቴክኖሎጂ እቃዎች ላይ ባደረገው የቁጥጥር ሥራ 583 የሚሆኑት የመረጃ እና መገናኛ ቴክኖሎጂ እቃዎች ለሀገር ደህንነት ስጋት በመሆናቸው ወደ ሀገር እንዳይገቡ ከልክሏል፡፡ አጠቃላይ በበጀት አመቱ 4,336 (አራት ሺ ሦስት መቶ ሰላሳ ስድስት) የሚሆኑ የመረጃ እና መገናኛ ቴክኖሎጂ እቃዎች ወደ ሀገር ለማስገባት ፈቃድ የተጠየቀባቸው ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ 1,143 የሚሆኑት የደህንነት ስጋት የሌለባቸው በመሆኑ ወደ ሀገር እንዲገቡ ፈቃድ ተሰጥቷል፡፡
በግለሰብም ሆነ በተቋማት ደረጃ ወደ ሀገር እንዲገቡ ያልተፈቀዱት የመረጃ እና የመገናኛ ቴክኖሎጂ ምርቶች ወደ ሀገር ገብተው ቢሆን ኖሮ በሃገር ሰላምና ደህንነት ላይ ትልቅ ስጋት ሊደቅኑ የሚችሉ የስለላ እና ወታደራዊ መሳሪያዎች በግለሰቦች እጅ ይወድቃሉ፤ ባልተፈቀደላቸው አካላት የሚደረግ የስለላ እና ክትትል መጠን ሊጨምር ይችላል፤ ቁልፍ የመንግስት እና የግል ድርጅቶች ደህንነታቸው አደጋ ውስጥ ይወድቃል፤ የመንግስት የመገናኛ መሳሪያዎች ይጠለፋሉ (Intruder Interception) እንዲሁም ታላላቅ የመንግስት የጸጥታ ተቋማት የመረጃ መሳሪያዎች ላልተፈቀደላቸው አካላት ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችሉ ነበር፡፡
በአጠቃላይ እነዚህ የመረጃ እና የመገናኛ ቴክኖሎጂ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው ቢሆን የፖለቲካ አለመረጋጋትን የሚፈጥሩ፣ ሽብርተኝነትን የሚያስፋፉ፣ በግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ ስጋት የሚሆኑ እና የሀገሪቱን ሰላም ከማደፍረስ አኳያ እኩይ ሚና ሊኖራቸው የሚችሉ ነበሩ፡፡
የመረጃ እና መገናኛ ቴክኖሎጂ እቃዎች (ጂፒኤስ፣ ከፍተኛ አቅም ያላቸው ካሜራዎች፣ የመገናኛ ሬዲዮኖች፣ ራውተሮች፣ ኮምፓሶች፣ ሰርቨሮች ወዘተ) አስመጪዎች ወይም ለድርጅታቸው አስፈላጊ ሆኖ ከውጪ ማስገባት የሚፈልጉ አካላት ቅድመ ፈቃድ አገልግሎት ለማግኘት www.esw.et/esw-trd አድራሻ በመጠቀም ሊያስመጡ ያቀዱትን የመረጃ እና መገናኛ የቴክኖሎጂ እቃዎች ዝርዝር መረጃ (specifications) በመላክ የቅድመ ፈቃድ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡ ይህም እቃውን ካስመጡ በኋላ ከሚደርስ ኪሳራና እንግልት ማስቀረት ይችላል፡፡
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በአዋጅ ከተሰጡት ተግባርና ሃላፊነቶች መካከል ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡና ከሀገር የሚወጡ የመረጃ እና መገናኛ ቴክኖሎጂ እቃዎች በሀገር ደህንነት ላይ ሊያስከትሉ የሚችሉትን አደጋ የመከላከልና የመቆጣጠር ሃላፊነት አንዱ ነው።
ወቅታዊና ተጨማሪ የሳይበር ደህንነት መረጃዎችን ለማግኘት፡-
 
ቴሌግራም፦ https://t.me/insagovet