በተቋሙ የተጀመሩትን ለዉጦች ዳር ለማድረስ የሁሉም አመራሮችና አባላት ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሀሚድ ገለጹ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

አዲስ አበባ፡ የካቲት 04/2016 ዓ/ም፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የሳይበር ደህንነት ተቋም የመገንባት ትልቅ ራዕይ ይዞ የተነሳውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) የሪፎርም ሥራ በማስጀመርና በመምራት ረገድ የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ የተጫወቱት የአመራርነት ሚና ወሳኝ እንደሆነ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ተናገሩ፡፡

የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ ከአስተዳደሩ አመራሮችና በአጠቃላይም ከአባላት ጋር በመሆን የጀመሩት ተቋማዊ የሪፎርም ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ለስኬት እንደሚበቃም ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር በመሆን የተሾሙት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ከቀድሞው የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ ጋር የሥራ ርክክብ አድርገዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ በኢመደአ የሪፎርም ጉዞና አጠቃላይ ተቋማዊ ተልዕኮ ስኬቶች ላይ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋናና እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡

የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ በመርሃ ግብሩ እንደገለጹት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከነበሩበት ዘርፈ ብዙና ውስብስብ ችግሮች አውጥቶ ተቋሙን በሚመጥን ደረጃ እና መንግስትና ሕዝብ ከዘርፉ የሚጠብቀውን አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል ጥልቅ የሆነ የሪፎርም ሥራ መሰራቱንና ስኬት ማስመዝገብ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

በተቋማዊ የሪፎርም ሥራ በቀዳሚነት የተልዕኮ ተጣጣሚነትን ማረጋገጥ ቁልፍ የሪፎርም አጀንዳ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ሰለሞን፤ ለዚህም እንደ ተቋም ውስጣችንን በሚገባ በመፈተሽ ያሉብንን ተግዳሮቶች የመለየትና በአግባቡ የመተንተን እንዲሁም ለችግሮቹ መፍትሄ የሚሆኑ የሪፎርም ኢኒሼቲቮችን በመቅረጽ ወደተግባር በመግባት ተጨባጭ ስኬቶችን ማስመዘገብ ጀምረናል ብለዋል፡፡

ለተቋማዊ የሪፎርም ሥራ ስኬት ቁልፉ የአመራርና የባለሙያ ልሕቀት ማረጋገጥ እንደሆነ በመገንዘብ ተልዕኮን በላቀ ደረጃ መወጣት የሚችል የአመራር ምደባ እንደተደረገ በሽኝት ፕሮግራሙ ላይ አቶ ሰለሞን ተናግረዋል፡፡

አዲስ የተሾሙት የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ቁልፍ ሃብት የሰው ሃይሉ እንደሆነ ገልጸው፤ ይህንን የአስተዳደሩን እምቅና ቁልፍ ሃብት በአግባቡ በመምራት የተቋሙ የሪፎርም ሥራ ጉዞ ከግብ እንዲደርስ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

ተቋሙ ወደ ሚገባዉ ደረጃ ገና አልደረሰም ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ የተጀመሩትን ለዉጦች ዳር ለማድረስ የሁሉም አመራሮችና አባላት ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

በመጨረሻም የተቋሙ ማህበረሰብ ከጎኔ እንደሚሆን አልጠራጠርም ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ትዕግስት ሀሚድ እጅግ በተሻለ ደረጃ የስራ ባህላችንን በማሳደግ ከመንግስት የተጣለብንን ሃላፊነት በሚገባዉ ልክ ልንወጣ ይገባናል ብለዋል።