የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶች የደህንነት ማረጋገጫና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ኃብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) በቀረበው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶች የደህንነት ማረጋገጫና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ኃብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በውይይቱ ላይ እንዳሉት የቀረበው ረቂቅ አስፈላጊ ግብአትና መሻሻል ታክሎበት ለሕዝብ ውይይት መድረክ እንደሚቀርብና በቀጣይ እንደሚጸድቅ ገልጸዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ የረቂቅ አዋጁ አስፈላጊነት በተመለከተ ባደረጉት ገለጻ ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶች ዕድገትና መራቀቅ ጋር ተያይዘው የሚመጡ አሉታዊ ተፅእኖዎች በሀገራዊ የኢንፎርሜሽን ሀብቶች ደህንነት እንዲሁም በዜጎች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ ጥቃቶችን አስቀድሞ መከላከልና መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡

አቶ ሰለሞን ሶካ አክለው እንደገለጹት ወደሀገር ውስጥ እንዳይገቡ የሚከለከሉ እና በገደብ የሚገቡ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶችን ለመለየት፣ የደህንነት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰጣጥ ስርአትን ለመወሰን እና በምርቶቹ ላይ ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ የሚያስችል ግልፅ፣ ወጥ እና ፍትሃዊ አሰራር መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱን አብራርተዋል፡፡

ረቂቅ አዋጁን አስመልክቶ ከሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት የሰው ኃብት ልማት፣ሥራ ሥምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ለተነሱ ማብራሪያ የሚፈልጉ ጥያቄዎች የአስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በቀጣይ የተሰጡ ጠቃሚ ግብአቶች ተጨምረውበት ይፋዊ የሕዝብ መድረክ እንደሚዘጋጅ በመድረኩ ተገልጿል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች