የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች የሳይበር ደህንነት ጉዳይን ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተጠቆመ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች እና የከተማ መስተዳድር ከንቲባዎቸ የሳይበር ደህንነት ጉዳይን ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተጠቆመ፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) 4ኛውን ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር በማስመልከት ባዘጋጀው የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ፣ ህግና ስታንዳርድ የግንዛቤ መፍጠሪያ የቪዲዮ ኮንፈረንስ (Virtual Conference) መድረክ ላይ የሁሉም ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች/ተወካዮች፣ የከተማ መስተዳድር ከንቲባዎች እንዲሁም የክልል የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

ኮንፈረንሱ በሳይበር ደህንነት ስጋቶች፣ የሳይበር ደህንነትን ለማረጋገጥ የተዘረጉ የአስተዳደር ማዕቀፎች ስለመፍጠር፣ እንደ ሀገር የሳይበር ደህንነት ስጋት ያለበትን ደረጃ ለማመላከት እና ለሳይበር አስተዳደር ማዕቀፎች አተገባበር አጋርነትና ትስስር መፍጠርን ዓላማ ያደረገ ነበር፡፡

የሳይበር ቴክኖሎጂ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለና በፍጥነት እየተስፋፋ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ከግለሰብ መብት ጥሰት ጀምሮ የሃገርን ደህንነትና ሉዓላዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ የሳይበር ወንጀሎችና ጥቃቶችም እየጨመሩ እንደሚመጡና ለዚህም ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት የህግ፣ የስታንዳርድና የፖሊሲ ማእቀፎች ማዘጋጀትና ተግባራዊ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን በውይይት መድረኩ ላይ ተገልጿል፡፡

በሳይበር ደህንነት ዘርፍ የሰለጠነ የሰው ሀይል እጥረት፣ የባለሞያዎች የአቅም ውስንነት፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክፍተት፣ የአሰራር ስርአት አለመኖር፣ በማህበረሱ ላይ የሚስተዋሉ የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ እጥረት ወ.ዘ.ተ የሳይበር ደህንነትን ለማረጋገጥ ትልቅ ተግዳሮቶች መሆናቸውን የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች አንስተዋል፡፡ ለዚህም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ክልሎችን ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ መደገፍ እንደሚጠበቅበት ገልጸዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ እንዳሉትክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች የዲጂታል 2025 ኢትዮጵያ ራዕይን እውን ለማድረግ ለሳይበር ደህንነት ጉዳይ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም ክልሎች የሳይበር ደህንነት የህግ፣ የፖሊሲና የስታንዳርድ ማእቀፎችን ተግባራዊ ለማድረግ ያለባቸውን የቴክኖሎጂ፣ የአሰራር ስርአት እና የሰው ሀይል አደረጃጀት ውስንነት ለመቅረፍ ቀጣይነት ባለው መልኩ በቅንጅት እና በትብብር ለመስራት አስተዳደሩ ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች