በ2023 እ.ኤ.አ በአፍሪካ በሞባይል ስልኮች ላይ የሚደርስ የሳይበር ጥቃት ቁጥር መጨመሩን ካስፐርስኪ ገለፀ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ካስፐርስኪ ኩባንያ ባደረገው ጥናት እንደ አውሮፓዊያኑ የዘመን አቆጣጠር በ2023 በሞባይል ስልኮች ላይ የሚደርሱ የሳይበር ጥቃቶች በአለማቀፍ ደረጃ እያደገ መምጣቱን ገልጿል፡፡ በጥናቱ መሰረት በ2023 በሞባይል ስልኮች ላይ የደረሱ የሳይበር ጥቃቶች ከ2022 ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ 5 በመቶ ጨምሯል፡፡

የካስፐርስኪ ኩባንያ ባወጣው ጥናት መሰረት ጥቃቱ የደረሰው በአብዛኛው በመካከለኛው ምስራቅ፣ ተርኪዬ እና አፍሪካ ውስጥ በካስፐርስኪ የተገኙ እና የታገዱ የአንድሮይድ የሞባይል ስልኮች ላይ መሆኑ ገልጿል፡፡

በሞባይል ስልኮች ላይ ከሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች መካከል የሞባይል ባንኪንግ ጥቃት ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዝ የጠቀሰው ጥናቱ፤ የሞባይል ባንኪንግ ትሮጃኖች ከኦንላይን ባንኪንግ እና ኢ-ክፍያ ስርዓት ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ለማደን የሚያገለግሉ የሞባይል ባንኪንግ ትሮጃኖች በስፋት መገኘታቸውን ጥቅሷል፡፡ በአፍሪካ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ተጠቃሚዎች የቅርብ ጊዜ የደህንነት ማሻሻያ የሌላቸው፣ ዝቅተኛ ደረጃ ያላቸው ወይም የቆዩ የሞባይል መሳሪያዎችን ይጠቀማሉ፣ ይህም ለሞባይል ስጋቶች የበለጠ ተጋላጭ ያደርጋቸዋል። ከዚህ አንጻር በሞባይል መሳሪያዎች ላይ የሳይበር ደህንነት መፍትሄዎችን መተግበር ብቻ ሳይሆን ተጠቃሚዎችን ስለ ምርጥ ተሞክሮዎች እና በፍጥነት እየተለዋወጠ ስላለው የአደጋ ገጽታ ማስተማርም እንደሚያስፈልግ ጥናቱ አመላክቷል።

ከዚህ አኳያ የፋይናንስ ተቋማትም የደንበኞቻቸውን የሳይበር ደህንነት ለመጠበቅ የቅደመ መከላከል እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን መስራት እንዳለባቸው ጠቁሟል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች