ላለፉት 30 ቀናት ስልጠና ወስደው ያጠናቀቁ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተመረቁ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ፣ በመከላከያ ሚኒስቴር እና በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ትብብር ላለፉት 30 ቀናት ስልጠና የወሰዱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ዛሬ ተመርቀዋል።

በምረቃ ስነስርአቱ ላይ የኢፌድሪ የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ ባስተላለፉት መልዕክት ምንም እንኳን አሁን ላይ ሀገራችን ጦርነት ላይ ብትሆንም እነዚህን መሰል ጦርነቶችን በድል ለመወጣት ከጠላቶቻችን ሊሰነዘሩ የሚችሉ ጥቃቶችን ቀድሞ ለመከላከል በኤሌክትሮ ማግኔቲክ ዲፌንስ ዘርፍ የሰዉ ሃይል አሰልጥኖ ወደ ስራ ማስገባት ፋይዳዉ ብዙ ነዉ ብለዋል።

ወደፊትም ሀገራችን በዘርፉ የበቁ የሰዉ ሀይል ለማፍራት ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በትብብር የምንሰራ ይሆናል ሲሉ ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሀም በላይ ተናግረዋል ።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ በበኩላቸው ላልፉት 30 ቀናት በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የተሰጠዉ የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር ስልጠና ከሀገራዊ ተልዕኮ በመነሳት የሀገራችንን በኤሌክትሮኒክስ ዲፌንስ ዘርፍ ያለዉን የሰዉ ኃይል ክፍተት ለመሙላት ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል።

ይህን መሰል ስልጠናዎችን በጋራ ማዘጋጀት በተቋማቱ መካከል ያለዉን የትብብር መንፈስ የሚያሳይ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የትብብራችንም መነሻ የመደመር እሳቤ ነዉ። በመደመር እሳቤ ዉስጥ ቀድሞ የተገኙ ድሎችንና ውጤቶችን የበለጠ የሚያሰፋ እንደሆነ ተናግረዋል።

አያይዘውም ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሰለሞን ሶካ ስልጠናው “እኔ” ከሚል የአስተሳሰብ ቅኝት “እኛ” ወደሚል እሳቤ ከፍ ያልንበት ነው ያሉ ሲሆን ከተናጠል ይልቅ በጋራ እና በትብብር የሚሰሩ ስራዎች ውጤታቸው ከሚጠበቀዉ በላይ መሆኑን የዛሬው ስልጠና አመላካች ነው ሲሉ አክለዋል።

አያይዘውም ዋና ዳይሬክተሩ በቀጣይም ከተቋማቱ ጋር በሌሎችም ዘርፎች በመደመር እሳቤ የምንሰራ ይሆናል ያሉ ሲሆን በይበልጥ በጸጥታ እና ደህንነት ተቋማት መካከል የሚመሰረት የመደመር እሳቤ የሀገር ሉአዊነትን እና የዜጎችን ክብር ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው ብለዋል።

የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ጉታ በበኩላቸዉ ጨዋታ ቀያሪ የኤሌክትሮኒክ ዋርፌር ቴክኖሎጂዎች አዲስና ውጤታማ እውቀት እና ክህሎት ያለው የሰው ሃይል ለመገንባት የተቀናጀ እና ተደማሪ ስራዎችን መስራት ይገባል። አያይዘውም ም/ዋና ዳይሬክተሩ በዚህም የኤሌክትሮማግኔቲክ፣ የዳይሬክትድ ኢነርጂ እና የተቀናጀ ሳይበር አቅም የጨዋታ ቀያሪ ኢንተለጀንስ እና ዋርፌር ተልዕኮዎችን ለመወጣት አቅም መገንባት ይጠይቃል ብለዋል።

መሰል ስልጠናዎችን መስጠት የሚያስችል ዝግጅት አጠናቀናል ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ዳንኤል ጉታ በቀጣይ ለሚኖሩ የአቅም ግንባታ ፕሮግራሞችና ቅንጅታዊ የልህቀት ፍላጎቶች በከፍተኛ ተነሳሽነትና ሀገራዊ ስሜት ምላሽ የምንሰጥ ይሆናል ሲሉ ጠቅሰዋል።