አፍሪካ የወጣቱን አቅምና ጠንካራ የስራ ፈጠራ መንፈስን በመጠቀም የሳይበር ምህዳሩ የፈጠረዉን መልካም እድሎች አሟጣ ልትጠቀም ይገባል ተባለ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በአፍሪካ ያለዉን ሰፊ የወጣት ሃይልና ጠንካራ የስራ ፈጠራ መንፈስ በመጠቀም የሳይበር ምህዳሩ የፈጠረዉን ዕድል አሟጦ መጠቀም እንደሚገባ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ "የሳይበር ደኅንነትን ማጎልበት ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት እና ከዚያ ባሻገር" በሚል ርዕስ በተካሄደዉ የፓናል ዉይይት ላይ ገለጹ።

ዋና ዳይሬክተሩ የሳይበር ምህዳሩን በጥንቃቄ መጠቀም ካልቻልን በንግድ እንቅስቃሴዎች፣ በሀገራዊ አጠቃላይ ኢኮኖሚ እና በብሔራዊ ደኅንነት ላይም ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል ሲሉ አራተኛ ቀኑን በያዘዉ ጄይቴክስ ግሎባል ኮንፈረንስ ላይ ተናግረዋል።

በተለይ አህጉራችን አፍሪካ ለሳይበር ጥቃት የተጋለጠች መሆኑዋን ያነሱት ሃላፊዉ አፍሪካ ከሌሎች በበለጠ የሳይበር ጥቃቱ ሰለባ የመሆኗ ምክንያት ደግሞ የቴክኖሎጂ ጥገኝነት የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ማነስ፣ የሀብት ውስንነት እና የመሠረተ ልማት ግንባታ አለመስፋፋት ዋና ዋና ምክንያቶች መሆናቸዉን አቶ ሰለሞን ጠቁመዋል።

ይሁን እንጂ አፍሪካ ነባራዊ  ሁኔታ በቴክኖሎጂና በሳይበር ደህንነትን ዘርፍ  ያላትን አቅም ለማሻሻል የሚረዱ በርካታ ጥንካሬዎች አሏት ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ከነዚህም  መካከል  ወጣት እና እያደገ የመጣ አምራች ሀይል፣ ጠንካራ የስራ ፈጠራ መንፈስ እና ቁርጠኝነትን እንደ ማሳያ አንስተዋል። 

የአፍሪካን በዘርፉ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትና ብሄራዊ ደህንነትን ለማረጋገጥ  በግዢና በድጋፍ በሚገኙ የቴክኖሎጂ ምርቶች ላይ ጥገኛ በመሆን ማረጋገጥ አይቻልም ብለዋል።

የአፍሪካ አገራት የቴክኖሎጂ ባለቤትነት በማረጋገጥ ያላቸዉን ሰፊ የወጣት ሀይል በማሰልጠንና በማብቃት፣ ልዩ ተስጥዎያላቸዉን ታዳጊዎች በመመልመልና በመደገፍ፣ ትብብሮችንና ትሥሥሮችን  በማጠናከር እንዲሁም አቅም በማሰባሰብ ብሄራዊ ጥቅማቸዉንና ብሄራዊ ደኅንነታቸዉን ማረጋገጥ ይገባቸዋል  ሲሉ በመድረኩ ላይ አንስተዋል።

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች