ሀገራት የሳይበር ወንጀሎችን ለመከላከል የተቀናጀና ጊዜዉን የሚመጥን አካሄዶችን መከተል እንደሚገባ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ተናገሩ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በቴክኖሎጂ ላይ ያለው ጥገኝነት እየጨመረ መምጣቱ ተከትሎ የሳይበር ወንጀል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሀገራት፣ተቋማትም ሆነ ግለሰቦች ትልቅ ስጋት መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ገልጸዋል። ይህን ያሉት በዩናይትድ አረብ ኢሚሬት ዱባይ እየተካሄደ ባለዉ ጂይቴክስ ግሎባል (GITEX GLOBAL) “የሳይበር ጥቃት አለም አቀፍ ኪሳራ” በሚል ርዕስ በተካሄደዉ የፓናል ዉይይት ላይ ነዉ።

በዓለም አቀፍ ደረጃም ሆነ እንደ ሀገር በቴክኖሎጂ ላይ ያለን ጥገኝነት እየጨመረ መመጣቱ ለሳይበር ወንጀለኞች የኔትዎርክ፣ የአፕሊኬሽኖችና ሲስተሞች ላይ ያሉ የጥቃት ተጋላጨነት ክፍተቶችን እንዲጠቀሙ ትልቅ የሚባል እድሎችን እንደፈጠረላቸዉ ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

የሳይበር ወንጀሎች በተቋማት ላይ ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራን ብቻ አድርሰዉ እንደማያልፉ የገለጹት ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ከገንዘብ ኪሳራዉ ባሻገር ተቋማቱ የህዝብን አመኔታ፣ መልካም ስም እና ዝናቸውን ሊያሳጣቸው እንደሚችልም ገልጸዋል። ከዚህ ከፍ ሲልም የሳይበር ምህዳሩን በመጠቀም የሚሰነዘሩ የስነ -ልቦና (የሳይኮሎጂካል) ጦርነቶች ሀገራትን ዋጋ እያስከፈለ መሆኑን አንስተዋል።

የሳይበር ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ በአይነትና በስፋት እያደገ በመምጣቱ ተቋማት ከሳይበር ወንጀል ጋር ተያይዘው የሚመጡ አደጋዎችን ለመቀነስ ሰውን ያማከለ አካሄድ መከተል እንደሚገባቸዉ በመድረኩ አንስተዋል። የኢትዮጵያን የመከላከል ተሞክሮ በመድረኩ ያነሱት ዋና ዳይሬክተሩ እንደ ሀገር ጥቃቶችን መከላከል የሚያስችሉ አዋጆችን፣ ደንቦችና እና ሌሎች የፖሊሲ አማራጮችን እየተተገበረ መሆኑን ጠቁመዋል።

ተለዋዋጭ በሆነዉ የሳይበር ምህዳር ዉስጥ ተቋማትና ግለሰቦች ከምህዳሩ አዳዲስ አዝማሚያዎች ጋር ተጣጣሚ በሆነ መልኩ በመስራት ሊደርስባቸዉ የሚችልን ሁሉን አቀፍ ኪሳራ መቀነስ እንደሚገባ ያነሱት ሃላፊዉ እንደ ሃገር ከጊዜዉ ጋር አብረዉ በሚሄዱ ዘርፎች ላይ ጥናትና ምርምርን በማድረግ መጻኢ ስጋቶች ላይ እየተሰራ ነዉ ብለዋል።

በዚሁ መድረክ የኢትዮጵያን የሳይበር ደህንነት ለማረጋገጥ እየተወሰዱ ያሉ የቴክኖሎጂ ባለቤትነት፣ ትሥሥሮችና ትብብሮች፣ የማህበረሰብ ንቃተ ህሊናና እነዚህን እየደገፉ ስላሉ ፖሊሲዎች አዋጆችና ደንቦች ጋር አያይዘዉ ያሉ ተሞክሮዎችን አቅርበዋል። በይበልጥ የማህበረሰቡን ንቃተ ህሊና ክፍ ለማድረግ ከተለመደዉ ስልት በመዉጣት በስነ -ጥበባዊ ስራዎች ለአብነት ያህልም አስተዳደሩ የሀገራችንን የሳይበር ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያደርገውን የሳይበር ውጊያ የሚያስቃኝ ፊልም በማሰራት ወደ ማህበረሰቡ መድረስ ጀምረናል ብለዋል።

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች