የኢመደአ አመራርና አባላት የሀገራችን የ2016 ዓ.ም የ10 ወራት የማክሮ ኢኮኖሚና የዘርፎች ዋና ዋና አፈፃፀም እና የ2017 የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ምክክር አደረጉ
የኢመደአ አመራርና አባላት የሀገራችን የ2016 ዓ.ም የ10 ወራት የማክሮ ኢኮኖሚና የዘርፎች ዋና ዋና አፈፃፀም እና የ2017 የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ምክክር አደረጉ
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) አመራርና አባላት የሀገራችን የ2016 ዓ.ም የ10 ወራት የማክሮ ኢኮኖሚና የዘርፎች ዋና ዋና አፈፃፀም እንዲሁም የ2017 የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ሰፊ ዉይይት አደረጉ።
ዉይይቱን የኢመደአ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ጉታ በንግግር የከፈቱ ሲሆን ኢመደአ እንደዚህ ያሉ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መወያየቱ አሁናዊ ሀገራዊ ሁኔታን ከመረዳት ባሻገር በሀገራዊ ልማቱ ላይ በጎ ሚናን እንዲጫወቱ የሚያስችል መሆኑ ጠቁመዋል።
ከዚህ ባሻገር እንደ መረጃና ደህንነት ተቋም በሀገራችን እየተደረጉ ስላሉ ሁሉን አቀፍ የልማት እንቅስቃሴዎች ሰፊ ግንዛቤ ሊኖረን እንደሚገባ አቶ ዳንኤል ጉታ ገልጸዋል።
የ2016 የ10 ወራት የማክሮ ኢኮኖሚና የዘርፎች ዋና ዋና አፈፃፀም እና የ2017 የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ የኢመደአ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ አስቴር ዳዊት ለአመራሩና አባላቱ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል።
የ2016 በጀት ዓመት 10 ወራት አፈጻጸምና የ2017 አቅጣጫ ሰፊ ገለጻና ማብራርያ በኋላ ከአመራሩና አባላት ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን በተነሱ ጥያቄዎች ላይ የአስተዳደሩ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች አቶ ዳንኤል ጉታ እና ወ/ሮ አስቴር ዳዊት ምላሽ ሰጥተዋል።