የፌስቡክ አካውንቶን ደህንነት ለመጠበቅ ሊወሰዱ የሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎች

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የፌስቡክ አካውንቶን ደህንነት ለመጠበቅ ሊወሰዱ የሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎች

  1. የይለፍ-ቃልዎን ደህንነት ማረጋገጥ

#_የፌስቡክ አካውንቶን ለሌላ ማንኛውም የኦንላይን አገልግሎት ላይ አይጠቀሙ፤

#_በፍፁም የይለፍ-ቃልዎን ለሌላ ሰው አያጋሩ፤

#_የሚጠቀሙበት የይለፍ-ቃል ለመገመት አዳጋች የሆነ፣ በፍጹም የእርሶን ስም እና የተለመዱ ቃላትን ያልያዘ ሊሆን ይገባል፤ እንዲሁም

#_የይለፍ-ቃልዎ በፍፁም ኢ-ሜይልዎን፣ የስልክ ቁጥሮን ወይም የልደት ቀንዎን የሚጠቀም መሆን የለበትም፤

  1. በፍጹም የሚያስሱትን ድረ-ገጽ መረጃ አያጋሩ

#_አጥቂዎች ፌስቡክ የሚመስል የሐሰት ገጽ ፈጥረው በኢ-ሜይል አድራሻዎና በይለፍ ቃልዎ እንዲገቡ ሊጠይቅዎ ይችላሉ፤

#_ሁልጊዜም መረጃ የሚያስሱበትን ድረ-ገጽ URL ትክክለኝነት ያረጋግጡ፤ አጠራጣሪ ነገር ሲያጋጥሞ www.facebook.com በማፈላለጊያው ላይ በመጻፍ ወደ ትክክለኛው የፌስቡክ  ገጽ ለመመለስ ይሞክሩ፤

#_በፍጹም ከሜታ /Meta/ ወይም ፌስቡክ የሚላክሎትን ኢ-ሜይል ለሌላ ሰው አያጋሩ፣ በተለይም ስለ አካውንቶ ምስጢራዊ መረጃዎችን የያዙ ከሆነ፤

#_ስለፊሺንግ ጥቃት እና ጠንካራ የይለፍ-ቃል አጠባበቅ ላይ ያለዎትን እውቀትና ግንዛቤ በየጊዜው ያሳድጉ፤

  1. ኮምፒውተሮን ለሌላ ሰው የሚያጋሩ ከሆነ የፌስቡክ አካውንቶን ዘግተው መውጣቶን /Log Out/ ማድረጎን አይዘንጉ፤

#_ዘግተው ሳይወጡ ኮምፒውተሮን ወይም መሣሪያዎን ያዋሱ ከሆነም ከርቀት እንዴት መውጣት /Log Out Remotely/ እንደሚችሉ ይወቁ፤

#_ከርቀት ለሌላ አካል ካዋሱት ኮምፒውተር ላይ ለመውጣት ወደፌስቡክ "Security and Login Setting" ሲገቡ ከዚህ በፊት ይገቡባቸው የነበሩ መሣሪያዎችን ዝርዝር የሚያቀርብልዎ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የሚፈልጉት መሣሪያ ላይ "Logout" የሚለውን ትዕዛዝ በመጫን መውጣት ይችላሉ፤

  1. ከማያውቋቸው ሰዎች የጓደኝነት ጥያቄ ሲላክልዎ አይቀበሉ

#_ጠላፊዎች ሰዎችን ለማጥመድ ሲፈልጉ ሀሰተኛ አካውንት ሊፈጥሩ ይችላሉ፤

#_የጠላፊዎች ጓደኛ መሆን ምን አልባት የእርሶን የፌስቡክ የፊት ገጽን /Timeline/ ሊበክሉ፣ የተለያዩ ጉዳዮችን በገጾ ላይ ሊያጋሩ ወይም በካይ መልዕክቶችን በመልዕክት መቀበያዎ ሊልክብዎት ይችላሉ፤

  1. ከበካይ ሶፍትዌሮች እራሶን ይጠብቁ

#_አጥፊ ሶፍትዌሮች ኮምፒውተሮ፣ ሰርቨሮ /Server/ ወይም የኮምፒውተር ኔትወርክ ላይ ጉዳት ሊጥሉ ይችላሉ፤

#_የተበከለ ኮምፒውተር ወይም መሣሪያ ምን ዓይነት ባህሪያት እንደሚያሳዩ እና እንዴት በካይ ሶፍትዌሮችን ማስወገድ እንደሚችሉ በሚመለከት ያለዎትን እውቀት ያዳብሩ፤

#_ማፈላለጊያዎትን በየጊዜው ያዘምኑ፣ አጠራጣሪ መተግበሪያዎችን እና የማፈላለጊያ ማስታወቂያዎችን ያስወግዱ፤

  1. አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያዎችን /Links/ ከሚያውቁት ጓደኛ ወይም ድርጅት እንኳ ቢላክልዎት ከመክፈት ይቆጠቡ

#_እነዚህ በፌስቡክ ወይም በኢ-ሜይል የሚላኩ ማስፈንጠሪያዎች /Links/ ሊሆኑ ይችላሉ፤

#_ፌስቡክ ወይም Meta የይለፍ-ቃሎን በኢ-ሜይል እንዲያስገቡ በፍጹም እንደማይጠይቅዎ ይወቁ፤

#_አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያ ሲያጋጥሞ ለፌስቡክ ሪፖርት /report it/ ያድረጉ፤

  1. ተጨማሪ የደህንነት መጠበቂያ መንገዶችን ይተግብሩ

#_ከማይታወቁ አድራሻዎችና መሣሪያዎች ወደ አካውንቶ የመግባት ሙከራ ሲደረግ የጥቆማ መረጃ እንዲደርሶ /get alerts about unrecognized logins/ ያድረጉ፤

#_ባለሁለት ደረጃ የማንነት ማረጋገጫ ዘዴ /Set up two-factor authentication/ ይጠቀሙ፤

#_ሌሎች የደህንነት ጉዳዮችን በተመለከተ የፌስቡክ Help & Support ላይ በመግባት ያለዎትን ግንዛቤ በየጊዜው ያሳድጉ፤