የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የሚዲያ ጉዳዮች ሃላፊ ታላል አል አዘሪ ጋር ተወያዩ

内嵌的应用

资产发布器

የኢመደአ የ2017 ዓ.ም የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ምዝገባ ተጀመረ

የኢመደአ የ2017 ዓ.ም የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ምዝገባ ተጀመረ 星期三, 7 五月 2025

የሞሮኮ ሮያል አርሚ ከፍተኛ ልዑክ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኘ

የሞሮኮ ሮያል አርሚ ከፍተኛ ልዑክ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኘ 星期五, 25 四月 2025

40 የሚሆኑ የሳይበር ታለንት ማዕከል ወጣት ሴቶች በዓለም አቀፉ “የወጣት ሴቶች የአይሲቲ ቀን” ላይ ተሳተፉ

40 የሚሆኑ የሳይበር ታለንት ማዕከል ወጣት ሴቶች በዓለም አቀፉ “የወጣት ሴቶች የአይሲቲ ቀን” ላይ ተሳተፉ 星期五, 25 四月 2025

ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ስነ ምህዳር ለመፍጠር ዓለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ

ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ስነ ምህዳር ለመፍጠር ዓለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ 星期一, 14 四月 2025

资产发布器

null የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የሚዲያ ጉዳዮች ሃላፊ ታላል አል አዘሪ ጋር ተወያዩ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የሚዲያ ጉዳዮች ሃላፊ ከሆኑት ታላል አል አዘሪ ጋር በሳይበር ደህንነት እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡

በዉይይቱም የሳይበር ቴክኖሎጂ ባለቤትነትን በማረጋገጥና በዘርፉ ያለዉን የሰዉ ሃይል እጥረት በመቅረፍ ረገድ በጋራና በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

ኢመደአ የኢትዮጵያን የሳይበር የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን ለማረጋገጥ እየሰራ ያለዉ ስራ ለሌሎች አፍሪካ አገራት ምሳሌ ሊሆን የሚችል መሆናቸዉን የጠቀሱት ታላል አል አዘሪ ይህ መልካም ተሞክሮ ወደ ሌሎች አፍሪካ አገራት መስፋት የሚገባዉ መሆኑን ገልጸዋል። አያይዘውም በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ከኢመደአ ጋር በሳይበር ደህንነት ዘርፍ በይበልጥ በታዳጊዎች የሳይበር ታለንት ልማት ላይ በትብብር መስራት ፍላጎት እንዳለዉ ሚስተር ታላል ገልጸዋል።

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በበኩላቸው ኢመደአ በሳይበር ቴክኖሎጂ ባለቤትነት እንዲሁም በሳይበር ታለንት ልማት ያካበተውን ተሞክሮ ለሌሎች የአፍሪካ ሐገራት ለማካፈል ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ሰለሞን ሶካ ከታላል አል አዘሪ ጋር ካደረጉት ውውይት ባሻገር ኢመደአ ሐገራዊ የቴክኖሎጂ እና የእውቀት ባለቤትነትን በማረጋገጥ ረገድ እየሰራቸው የሚገኙ ሥራዎችን፤ የኢትዮ ሳይበር ታለንት ልማት ማዕከልን፤ እና ሌሎች ተቋማዊ ምርትና አገልግሎቶችን አስጎብኝተዋቸዋል፡፡