40 የሚሆኑ የሳይበር ታለንት ማዕከል ወጣት ሴቶች በዓለም አቀፉ “የወጣት ሴቶች የአይሲቲ ቀን” ላይ ተሳተፉ
40 የሚሆኑ የሳይበር ታለንት ማዕከል ወጣት ሴቶች በዓለም አቀፉ “የወጣት ሴቶች የአይሲቲ ቀን” ላይ ተሳተፉ
ዓለም አቀፉ የወጣት ሴቶች የአይሲቲ ቀን በአፍሪካ ህብረት አዳረሽ "ወጣት ሴቶች በኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) ለአካታች ዲጂታል ለውጥ" በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።
በፕሮግራሙ ለሁለት ወር በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአለም አቀፉ የቴሌ-ኮሚዩኒኬሽን ህብረት ITU) ጋር (በመተባበር በኦንላይን የተሰጠዉን ስልጠና ወስደዉ ያጠናቀቁ 40 የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) የታለንት ማዕከል ታዳጊ ሴቶች ተሳትፈዋል።
አስተዳደሩን በመወከል ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የኮምፒዉቲክና አናልቲግ ማዕከል ዳይሬክተር ሰብለ ኃይሉ (PhD) የህይወት ተሞክሯቸዉን ለወጣት ሴቶች አካፍለዋል።
በሥነ ሥርዓቱ ላይ የተለያዩ ስኬታማ ሴቶች ተሞክሯቸዉን ያቀረቡ ሲሆን በመድረኩ የተገኙት የአፍሪካ ቀጣናዊ አይቲዩ (ITU) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኢማኑኤል ማናሴ ይህ ስልጠና በዲጂታል ኢኮኖሚው የሴቶችን ተሳትፎ ከፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡