የሞሮኮ ሮያል አርሚ ከፍተኛ ልዑክ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኘ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በሞሮኮ ሮያል አርሚ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሃመድ በሪድ የተመራ የሞሮኮ ሮያል አርሚ ከፍተኛ ልዑክ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጉብኝት አደረገ፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ለልዑካን ቡድኑ አቀባበል ያደረጉ ሲሆን፤ የኢትዮጵያን የሳይበር ደህንነት በማረጋገጥ በኩል አስተዳደሩ በቴክኖሎጂ፣ በሰው ኃይል ልማት እና በአሰራር ስርአት እየሰራቸው የሚገኙ ሥራዎችን ገለጻ አድርገዋል፡፡ በቀጣይም የሁለቱን ሀገራት የሳይበር ደህንነት በማረጋገጥ ረገድ ሁለቱ ተቋማት በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

ኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነት እና ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ የሚያስችል ብቁና ዘመናዊ ተቋም መገንባት መቻሏን ልዑካን ቡድኑ በጉብኝታቸው ወቅት ገልጸዋል፡፡ ከዚህ አኳያ ልዑካን ቡድኑ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ያደረገው ጉብኝት ኢትዮጵያ እና ሞሮኮ በዲፕሎማሲው መስክ ያላቸውን ወዳጅነት ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገርና በሳይበር ደህንነት መስክም ይሁን በሌሎች መስኮች በጋራ ለመስራት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

ልዑካን ቡድኑ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በነበረው ጉብኝት የተቋሙን ምርትና አገልግሎቶች፣ የሳይበር ታለንት ልማት ማዕከል፣ እና ሌሎች የአስተዳደሩን ሥራዎች ጎብኝተዋል።

资产发布器


የቅርብ ዜናዎች