ኢመደአ እና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጋራ በሚሰሩባቸዉ ጉዳዮች ላይ ምክክር አደረጉ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) እና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጋራ በሚሰሩባቸዉ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አደረጉ።

በምክክር መድረኩ ላይ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ እና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ዓለምአንተ አግደውን ጨምሮ የየተቋማቱ ሌሎች ከፍተኛና መካከለኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

በዉይይቱ ወቅት የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ እንደገለጹት የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዜጎችን የፍትህ ስርዓት ተደራሽነት ለማስፋትና ራሱን በቴክኖሎጂ ለማዘመን በሚያደርጋቸዉ ማንኛዉም እንቅስቃሴዎች የኢመደአ ድጋፍ እንደማይለያቸዉ ተናግረዋል።

በይበልጥ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሊተገብራቸዉ ያሰባቸዉ የፍትህ ጉዳይ አስተዳደር ሲስተም እና ኤሌክትሮኒክ የሰነድ አስተዳደር ስርዓት የፍርድ ቤቶችን የአሰራር ስርዓት ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ በማድረግ ጉልህ ሚና እንደሚኖረዉ ዋና ዳይሬክተሯ ጠቁመዋል።

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ዓለምአንተ አግደው በበኩላቸዉ የአማራ ክልል ከክልሉ ስፋትና የማሀበረሰቡ ለፍትህ ያለዉ በጎ አረዳድ ከፍተኛ መሆኑን አንስተዉ የፍርድ ቤቶችን አሰራር በቴክኖሎጂ መደገፍ ዜጎች በፍርድ ቤቶች አሰራር ላይ ያላቸውን እምነት ለመጨመር ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በጋራ ለመስራት የተደረገው ውይይት የክልሉን የፍትሕ ስርአት በማዘመንና ቀልጣፋ በማድረግ የማሕበረሰቡን ፈጣን የሆነ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ነው ብለዋል።

ክቡር አቶ ዓለምአንተ አግደውን ጨምሮ ሌሎች የፍርድ ቤቱ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች የኢመደአን የቴክኖሎጂ ውጤቶች፣ አገልግሎቶችና የታለንት ልማት ማዕከልን ጎብኝተዋል።

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች