ስለ “የኮምፒዩተር ወንጀል አዋጅ” ምን ያህል ያውቃሉ?

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በሥራ ላይ ያሉ የሀገራችን ሕጎች ከአዳዲስ የቴክኖሎጂ ለውጦች ጋር በበቂ ሁኔታ ተጣጥመው የማይሄዱ እና የኮምፒዩተር ወንጀልን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር፣ ለመመርመርና ተጠርጣሪዎችን ወደ ፍትህ ለማቅረብ የሚያስችሉ ባለመሆናቸው፤ በአጠቃላይም የኮምፒዩተር ወንጀልን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር፣ ለመመርመርና ኤሌክትሮኒክ ማስረጃዎችን ለመሰብሰብ የሚያስችሉ አዳዲስ ስልቶችንና ሥርዓቶችን በሕግ መደንገግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ “የኮምፒዩተር ወንጀል አዋጅ” በ2008 ዓ/ም መውጣቱ ይታወቃል፡፡

አዋጁ ከወጣባቸው ጉዳዮች መካከልም አንዱ የዜጎችን የግል ነፃነት አደጋ ላይ ሊጥሉ ለሚችሉ የተለያዩ የኮምፒዩተር ወንጀሎች እና ሌሎች ከደህንነት ስጋቶች ጋር በተያያዘ የኢንፎርሜሽንና የኮምኒዩኬሽን ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ተገቢ ጥንቃቄና ጥበቃ ሊደረግለት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው፡፡

የኮምፒዩተር ወንጀል አዋጅ በሃገራችን ሥራ ላይ ከዋለ ከሰባት አመታት በላይ ቢሆነውም ዜጎች በአዋጁ ዙሪያ ተገቢው ግንዛቤ ኖሯቸው በመጠቀም ረገድ ውስንነቶች አሉ፡፡

አዋጁ በኮምፒዩተር ሥርዓትና በኮምፒውተር መሠረተ ልማትና ዳታ ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፤ በኮምፒዩተር አማካኝነት የሚፈፀሙ የማጭበርበር፣ የማታለል እና የስርቆት ወንጀሎች እንዲሁም በኮምፒዩተር የሚፈፀሙ የይዘት እና ሌሎች ተያያዥ ወንጀሎችን እና የምርመራና የቅጣት አይነቶችን በተመለከተ ሰፋፊ ማብራሪያዎችን አስቀምጧል፡፡

በኮምፒዩተር ወንጀል አዋጅ ዙሪያ ያለዎትን ግንዛቤ ለማሳደግ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም የአዋጁን ሙሉ ቅጂ እንዲያነቡ እንጋብዝዎታለን፡፡

https://insa.gov.et/.../%E1%88%B0%E1%8A%90%E1%8B%B6%E1%89%BD

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች