የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለ 1ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የእስልምና እምነት ተከታዮች 1ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ በእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸዉ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርአት የሚከበረው የዒድ አልፈጥር በዓል የሠላም፣ የፍቅር፣ የደስታና የመረዳዳት በዓል እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

ሕዝበ ሙስሊሙ በታላቁ የረመዳን ጾም ያሳየውን የመረዳዳትና የመተዛዘን ድንቅ እሴት በማስቀጠል ለተቸገሩና የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ያለንን በማካፈል በዓሉን አንድ ሆነን በደስታና በፍቅር ልናከብር ይገባል ሲሉ አቶ ሰለሞን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ባለፉት አመታት በሀገራችን ትልቅ አገራዊ ፋይዳ ያላቸውን የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በማቀድ፣ በአግባቡ መርቶ በማሳካትና አስደናቂ ውጤት በማምጣት ረገድ ስኬታማ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ የተለያዩ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ተግዳሮቶችን ተቋቁመን እንደሀገር የተመዘገበው ዕድገት ተስፋ ሰጪና ብልጽግናችን እውን እንደሚሆን ማረጋገጫ ነው ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም ከውስጥም ይሁን ከውጭ የሚደርስብንን ጫና ለመቋቋምና የሀገራችንን ህልውና በማስቀጠል ብልጽግናችንን ለማረጋገጥ ወሳኙ ውስጣዊ ጥንካሬያችን ነው ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ አኳያ ሕዝበ ሙስሊሙ ሕብረብሄራዊ አንድነታችንን በማጽናት ረገድ ወሳኝ ሚናውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በመጨረሻም የታላቁን የዒድ አልፈጥር በዓል ስናከብር በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ከቤት ንብረታቸው እና ከቄያቸው ተፈናቀለው ለሚገኙ ወገኖቻችን አስፈላጊውን ስነ ልቦናዊ፣ ብሎም ቁሳዊ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ቀጣይነት ባለው መልኩ የማገዝ፣ ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን ያለንን በማካፈል ሊሆን ይገባል ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሰለሞን ሶካ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

እንኳን ለ 1ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

ዒድ ሙባረክ!