የተቋሙ የሩብ ዓመት አፈጻጸም በጣም ከፍተኛ መሆኑን የዉጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ
የተቋሙ የሩብ ዓመት አፈጻጸም በጣም ከፍተኛ መሆኑን የዉጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ
በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን (ኢመደአ) የ2016 የመጀመሪያ ሩብ አመት የስራ ክንዉን የላቀ አፈጻፀም መሆኑን ገለጸ።
ይህን ያሉት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አሰተዳደር የ3 ወራት የስራ አፈጻጸም በገመገሙበት ወቅት ነዉ።
የተቋሙን የሩብ ዓመት አፈጻጸም የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት ለቋሚ ኮሚቴዉ አቅርበዋል።
ከሪፖርቱ በመነሳት ከቋሚ ኮሚቴዉ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ከቋሚ ኮሚቴዉ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች የኢመደአ ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች ምላሽ ሰጥተዋል።
ቋሚ ኮሚቴዉ ከቀረበዉ ሪፖርት በመነሳት የተሠሩ ሥራዎችን በአካል በመገኘት የጎበኙ ሲሆን በማጠቃለያዉ የኢመደአ የሩብ ዓመት አፈጻጸም በጣም ከፍተኛ መሆኑን የዉጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ ፈቲሂ ማህዲ(ዶ/ር) ገልጸዋል።
በጥንካሬ ከታዩና ከፍተኛ አፈጻጸም እንዲገኝ ካደረጉ ስራዎች መካከል የሀገራችንን የቴክኖሎጂ ባለቤት ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ፣የሳይበር ጥቃትን የመከላከል አቅም፣ አለም አቀፍ ትብብሮችን ከማጠናከር እና ምቹ የሰራ ከባቢን ከመፍጠር አንጻር የተሰሩ ስራዎች ይገኙበታል።
በቀጣይ የታዩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል እና ክፍተቶችን በማስተካከል ከዚህ የበለጠ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ የተከበሩ ፈቲሂ ማህዲ (ዶ/ር) አመካክተዋል።
በተለይም የተቋሙን የትኩረት መስኮች ለማሳካት የራሱን ገቢ የማመንጨት ፣ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርና መሰል ወንጀሎችን የመከላከል፣ በሰው-ሀብት ልማትና አስተዳደር በኩልም የረጅም፣ የመካከለኛና የአጭር ጊዜ ስልጠናዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሠራ እና በግብረ መልሱ የተመላከቱት ጉዳዮች እንዲያጤኑ ምክትል ሰብሳቢዉ አሳስበዋል፡፡