የክሪፕቶከረንሲ ማይኒንግ ኢንዱስትሪን ለሀገር ልማት ማዋል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደኀንነት አስተዳደር (ኢመደአ) “ክሪፕቶከረንሲ ማይኒንግ ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያበሚል ርዕስ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱ ከክሪፕቶከረንሲ ማይኒንግ ኢንዱስትሪ ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ የሚያሳይ ጽሑፍ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ከኢንዱስትሪው ጋር ተያይዘው ሊመጡ የሚችሉ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ቀንሶ ዘርፉን ለልማት በመሚጠቅም መንገድ ጥቅም ላይ ማዋል በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ምክክር ተደርጓል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ፤ ክሪፕቶከረንሲ በአሁኑ ሰዓት በዓለማችን ላይ እየተስፋፉ ከመጡ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች መካከል አንዱና ዋነኛው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ክሪፕቶከረንሲ ለሀገር ልማትና ዕድገት የሚጠቅሙ በርካታ አዳዲስ ገጸ በረከቶችን ይዞ የመጣ ቢሆንም ከቴክኖሎጂው ባህሪይ የተነሳ በዚያው ልክ ተያያዥ የጎንዮሽ ጉዳቶች ያሉት በመሆኑ ጥንቃቄን የሚሻ ጉዳይ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

በተለይም የሀገራት ተቀዳሚ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳይ እየሆነ ከመጣው የሳይበር ደህንነት ጋር በተያያዘ ክሪፕቶከረንሲ ይዞት የሚመጣው የራሱ የሆነ አሉታዊ ውጤት አለው፡፡ ከዚህ አኳያ አሉታዊ ጎኑን ቀንሶ ኢንዱስትሪውን ለሀገር ለልማትና ዕድገት ለማዋል የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ትብብርና ቅንጅታዊ አሠራር የሚጠይቅ በመሆኑ ምክክርና ውይይት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ መድረኩ መዘጋጀቱንም አስገንዝበዋል፡፡

ቀጥሎም በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የብሎክቼይን ኤክስፐርት አቶ ናኦል ብርሃኑ ለውይይት መነሻ የሚሆን ጽሑፍ ቀርቧል፡፡ አቅራቢው የክሪፕቶከረንሲ ማይኒንግ ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ያለበትን ተጨባጭ ሁኔታ በጽሑፋቸው ዳስሰዋል፡፡ የሌሎች ሃገራት ተሞክሮ ምን እንደሚመስልም አሳይተዋል፡፡ የክሪፕሮከረንሲ ማይኒንግ ኢንዱስትሪ የራሱ የሆኑ አሉታዊ የጎንዮሽ ችግሮች ያሉበትና ትልቅ አቅም የሚጠይቅ ኢንቨስትመንት ቢሆንም እነዚህን ጉዳዮች ታሳቢ አድርጎ ከተሠራበት የውጭ ምንዛሬ ገቢ ማስገኘት፣ የሥራ ዕድልና የቱሪስት መስህብ መፍጠር ጨምሮ በርካታ ለሀገር ዕድገት የሚጠቅሙ መልካም ዕድሎችን ይዞ የሚመጣ መሆኑንም በጽሑፋቸው አመላክተዋል፡፡

ይሁን እንጅ ዘርፉ ትልቅ የደህንነት ስጋት ያለበት በመሆኑ ከፍተኛ የሆነ የባለድርሻ አካላትን ቅንጅትና ትብብር የሚጠይቅና ተገቢ የሕግና የቴክኖሎጂ ቁጥጥር ማዕቀፍ ማዘጋጀት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑንም የብሎክቼይን ኤክስፐርቱ አስገንዝበዋል፡፡ለዚህም ዘርፉን በበላይነት የመምራት ኃላፊነት የተሰጠው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ስለሆነም ኢመደአ ከአምስት ዓመታት በላይ የምርምርና ስርጸት ሥራዎችን ሲሠራ መቆየቱንና በመጨረሻም ኢንዱስትሪውን በአግባቡ አቀናጅቶ ለመምራት የሚያስችል መመሪያ 49/2023 የተባለ የሕግና የቴክኖሎጂ ቁጥጥር ማዕቀፍ መዘጋጀቱንም አመላክተዋል፡፡

በዘርፉ ዋነኛ ባለድርሻ አካላት ከሆኑትና ለክሪፕቶከረንሲ ማይኒንግ ኢንቨስትመንት የሚያስፈልገውን የኤሌክትሪክ ኃይል የማቅረብ ኃላፊነት የተጣለበት የኢትዮጵያ ኤሌክተሪክ ኃይል የገበያና ቢዝነስ ልማት ዳይሬክተር አቶ ሕይወት እሸቱ በበኩላቸው ከመሥሪያ ቤታቸው አኳያ ያለውን ዝግጁነትና አሁናዊ ሁኔታ የሚያስዳስስ ጽሑፍ ለመድረኩ አቅርበው ተጨማሪ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በመጨረሻም በቀረቡት የመነሻ ጽሑፎች ላይ በመድረኩ የታደሙት ባለድርሻ አካላት ሰፊ ውይይት ካደረጉባቸው በኋላ የኢመደአ ምክትል ዋና ዳይሬክተር / ትዕግስት ሃሚድ ማጥዕቃለያ ሰጥተዋል፡፡ በማጠቃለያቸውም ኢንዱስትሪውን ይበልጥ አጠናክሮ በቅንጅት ለመምራትና ሀገሪቱ ከዘርፉ በአግባቡ ተጠቃሚ የምትሆንበትን ዕድል ለመፍጠር ተጨማሪ ውይይትና ምክክሮች ሊደረጉ እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች