የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር 3ኛዉን የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ አስጀመረ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) 3ኛውን የሳይበር ደህንነት የሰመር ካምፕ ፕሮግራም በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አስጀመረ። በሰመር ካምፕ[ ፕሮግራሙ ከመላው የኢትዮጵያ ክፍል የተውጣጡ በቁጥር ሦስት መቶ (300) ታዳጊ ወጣቶች ተሳታፊ እንደሆኑ በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል፡፡

በሰመር ካምፕ የማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ እንደገለጹት ኢመደአ ተቋማዊና ሀገራዊ ተልዕኮውን በብቃት ለማሳካትና ቀጣይነት ያለው ሀገራዊ የኢንፎርሜሽን ደህንነትን ለማረጋገጥ የታዳጊዎችን ታለንት ወጥ በሆነ መንገድ መመልመል፣ ማልማት እና መጠቀም ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ በመገንዘብ ከተቋሙ ምስረታ ጀምሮ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።

የዲጂታል እድገት ይዞት የመጣውን ዕድል ለሀገር ልማትና ዕድገት ለማዋል በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ልዩ ተሰጥዖ ያላቸውን ታዳጊ ወጣቶችን መለየትና ማብቃት ወሳኝ መሆኑን ያነሱት ዋና ዳይሬክተሯ፤ በዚህ ረገድ ኢመደአ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ የሳይበር ታለንት የሰመር ካምፕ ፕሮግራም በየአመቱ በማዘጋጀት ሥልጠናዎችን እየሰጠ መሆኑን አስታውሰዋል።

በዚህም በ2016 ዓ.ም ለሦስተኛ ጊዜ የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ማዘጋጀቱን ገልጸው፤ በተለይም የዘንድሮው የሰመር ካምፕ ፕሮግራም ካለፉት ሁለት አመታት ከተዘጋጁት ፕሮግራሞች በቁጥርም ሆነ በተደራሽነት ከፍ ያለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የ3ኛ ዙር የሰመረ ካምፕ ተሳታፊዎች በሰመር ካምፕ መርሃ ግብሩ ከሚሰጣቸው ስልጠና ባሻገር በሀገር አቀፍ ደረጃ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በይፋ የተጀመረዉን “የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ” ስልጠናዎችን በመውሰድ ፋና ወጊ መሆናቸውን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ይህንንም መነሻ በማድረግ ሌሎች የኢትዮጵያ ታዳጊ ወጣቶች የኢኒሼቲቩ አካል እንዲሆኑና ስልጠናዎችን እንዲወስዱ አምባሳደር በመሆን ሊሰሩ እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በሰመር ካምፕ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደረጀ እንግዳ በበኩላቸው የዩኒቨርሲቲው ዋና ተልዕኮ የሆነውን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ስርፀት ሥራ በአግባቡ በማከናወን ረገድ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በጋራ መስራት ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም በሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ፕሮግራምም ይሁን በሌሎች መሰል ፕሮግራሞች ላይ ከኢመደአ ጋር ያላቸውን ቅንጅታዊ ሥራ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ በሰመር ካምፕ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከስተመር ኤክስፔሪያንስ ም/ፕሬዚዳንት አቶ ኃየለእየሱስ በቀለ ባስተላለፉት መልዕክት በተለያዩ ዘርፎች ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት የሚታወቀው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሃገር ትልቅ አስተዋፅኦ የሚያበረክቱ የፈጠራ ሥራዎችንም በፋይናንስ ይደግፋል ብለዋል፡፡

በዚህም ኢመደአ የጀመረውን የሳይበር ታለንት ልማት ፕሮግራም በቀጣይነት በመደገፍና በጋራ በመስራት ለዘርፉ እድገት የበኩላችንን ሚና እንወጣለን ብለዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በ2014 ዓ.ም ባካሄደው የመጀመሪያ ዙር የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ፕሮግራም 60 ታዳጊ ወጣቶችን፤ በ2015 ባካሄደው ሁለተኛ ዙር ደግሞ 120 ታዳጊ ወጣቶች አሰልጥኖ አስመርቋል፡፡

ዘንድሮም በ2016 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ በተከናወነ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ፕሮግራም ከተመዘገቡ ከ6 ሺ በላይ ባለ ልዩ ተሰጥኦዎች መካከል የተለያዩ ፈተናዎችን በማለፍ በቁጥር ሦስት መቶ (300) የሚሆኑ ባለ ልዩ ተሰጥዎ ታዳጊ ወጣቶች የሰመር ካምፕ ፕሮግራሙ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡