የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕን የውስጥ አሠራር ለማዘመን የሚያስችል የስራ ዉል ስምምነት ተፈራረመ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የውስጥ አሠራሩን ለማዘመን የሚያስችለውን የስራ ዉል ስምምነት ሰነድ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ጋር ተፈራርሟል፡፡

የመግባቢያ ሰነዱ በተፈረመበት ወቅት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ እንደገለጹት፤ ሥራን በአግባቡ ለማከናወንና ተልእኮን ለማሳካት ተገቢውን የሰው ኃይል ማሟላትና ለዚሁ የሚመጥን የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሰው ኃይሉና የተዘረጋው የአሠራር ሥርዓት ውጤታማ የሚሆነውና ሥራውንም በአግባቡ ማከናወን የሚችለው ደግሞ አስቻይ የሆነው ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ሲውል መሆኑን ያመላከቱት አቶ ሰለሞን፤ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕን ዘመኑ የሚዋጀውን ቴክኖሎጂ ለማስታጠቅና አሠራሩን በዘመናዊ መንገድ የሚከውንበትን ሥርዓት ለመዘርጋት ተስማምተናልብለዋል፡፡

ከዚህ አኳያ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ አሠራሩን ለማዘመን ሃገር በቀል ተቋም የሆነውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን መምርጡ ተገቢና ብልሃት የተሞላበት ውሳኔ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለንያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ሥራው አንድ ዓመት ተኩል ድረስ የሚወስድ ቢሆንም ከዚያ ባጠረ ጊዜ ውስጥ ለሌሎችም ተቋማት ምሳሌ መሆን የሚችል የውስጥ አሠራርን የማዘመን ሥራ በከፍተኛ ጥራት ሠርቶ ለማስረከብ በትኩረት የሚሠራ መሆንም ገልጸዋል፡፡

የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ ከኢመደአ ጋር የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ የተቋማቸውን የአሠራር ሥርዓት ለማዘመንና የተጀመረውን የሪፎርም ሂደት ለማሳካት የሚያስችል ነው፡፡

የስራ ዉል ስምምነቱ ንብረታችንና የሰው ሃብታችን ከብክነት ለማዳንና ብሎም ቀልጣፋና ዘመናዊ አሠራር ለመዘርጋት የሚያስችል ነውያሉት አምባሳደር ሱሌይማን፤ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዘመናዊ አሠራር ሥርዓትን በመዘርጋት የዳበረ ልምድ ያለው ሃገር በቀል ተቋም በመሆኑ ምርጫቸው ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በሌሎች የውጭ ሃገር ተቋማት ሥራውን ለማሠራት ተሞክሮ የነበረ መሆኑን ያመላከቱት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ ሆኖም ከደህንነት አኳያም የሃገር በቀል ተቋም ተመራጭ በመሆኑ በኢመደአ አማካኝነት ለማሠራት መወሰኑን ተናግረዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በበኩላቸው፤ ሥራን በአግባቡ ለማከናወንና ተልእኮን ለማሳካት ተገቢውን የሰው ኃይል ማሟላትና ለዚሁ የሚመጥን የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሰው ኃይሉና የተዘረጋው የአሠራር ሥርዓት ውጤታማ የሚሆነውና ሥራውንም በአግባቡ ማከናወን የሚችለው ደግሞ አስቻይ የሆነው ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ሲውል መሆኑን ያመላከቱት አቶ ሰለሞን፤እኛም ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕን ዘመኑ የሚዋጀውን ቴክኖሎጂ ለማስታጠቅና አሠራሩን በዘመናዊ መንገድ የሚከውንበትን ሥርዓት ለመዘርጋት ተስማምተናልብለዋል፡፡

ከዚህ አኳያ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ አሠራሩን ለማዘመን ሃገር በቀል ተቋም የሆነውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን መምርጡ ተገቢና ብልሃት የተሞላበት ውሳኔ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡እኛም ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለንያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ሥራው አንድ ዓመት ተኩል ድረስ የሚወስድ ቢሆንም ከዚያ ባጠረ ጊዜ ውስጥ ለሌሎችም ተቋማት ምሳሌ መሆን የሚችል የውስጥ አሠራርን የማዘመን ሥራ በከፍተኛ ጥራት ሠርቶ ለማስረከብ በትኩረት የሚሠራ መሆንም ገልጸዋል፡፡