3ኛው ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር በስኬት ተጠናቀቀ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የተቀናጀ የሳይበር ደህንነት ለሃገር ሉዓላዊነት በሚል መሪ ቃል ከጥቅምት 1 – 30 /2015 ዓ/ የተካሄደው 3ኛው ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር በስኬት መጠናቀቁን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ ገለጹ፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ 3ኛው የሳይበር ደህንነት ወር መጠናቀቅን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫቸውም 3ኛው የሳይበር ደህንነት ወር ባለፉት ሁለት አመታት ከተከበሩት የሳይበር ደህንነት መርሃ ግብሮች ጋር ሲነጻጸር በበርካታ መመዘኛዎች ስኬታማ እንደነበር አብራርተዋል፡፡ በዚህም ከቆይታ፣ የምክክር መድረኮች ብዛት፣ የተሳታፊ ተቋማት እና አጋር ድርጅቶች ስብጥር፣ ከተደራሽነት እና ከወጪ አንፃር በንፅፅር ከባለፉት ሁለት የሳይበር ደህንነት መርሃ ግብሮች አንጻር ስኬታማ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አመላክተዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተ አቶ ሰለሞን ሶካ አያይዘውም በዘንድሮው የሳይበር ደህንነት ወር ከ320 በላይ የግልና የመንግስት ተቋማትን ማሳተፍ እንደተቻለ ገልጸዋል፡፡ በሌላም በኩል በዲጂታል ሚዲያዎች በተፈጠረ ትስስር፣ በሜንስትሪም ሚዲያዎች እና በሬዲዮ በተሰሩ የተለያዩ ፕሮግራሞች፣ በህዝብ ትራንስፖርቶችና አደባባዮች በተሰራጩ መረጃዎች እና በህትመት ሚዲያዎች አማካኝነት ከ50 ሚሊበላይ ዜጎችን መድረስ እንደተቻለና የሳይበር ደህንነት ንቃተ ህሊናና ግንዛቤ መፍጠሪያ መልዕክቶችን ማስተላለፍ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

በ3ኛው የሳይበር ደህንነት ወር አራት አበይት መድረኮች ተፈጥረው እንደነበር የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ በእነዚህ መድረኮችም የሚፈለገውን ውጤት ማግኘት መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

በመጀመሪያው ሳምንት በተፈጠረው መድረክ  ከግል ተቋማት፣ ከሲቪክ ማህበራት እና አጋር ድርጅቶች ጋር በተደረገ ምክክር በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ያሉ ማነቆዎችን፣ የፖሊሲ አማራጮችን ብሎም አቅምን መፈተሽ እና ትውውቅ መፍጠር መቻሉን አቶ ሰለሞን ሶካ ገልፀዋል፡፡

በሁለተኛው ሳምንት መርሃ ግብር ተቋማት ከሳይበር ጥቃት ታጋላጭነት አንፃር እራሳቸውን የፈተበት ሲሆን በዘርፉ የተሰማሩ ሁራን ጥናትና የምርምር ስራዎቻቸውን ያቀረቡበት እንደነበር ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

በሶስተኛው ሳምንት የሳይበር ደህንነት ወር በተካሄደው መድረክ በሳይበር ደህንነት ዘርፍ የሚታየውን የሰው ኃይል እጥረት ከመቅረፍ አንፃር የትምህርት ተቋማት በካሪኩለም ቀርፀው የሳይበር ደህንነት ትምህርትን እንዲያስተምሩ የጋራ ምክክር ተደርጓል፡፡ ከዚህም ባሻገር ዘርፉን ለማበረታታት የግል እና የመንግስት ተቋማት በፋይናንስ ድጋፍ እንዲያደርጉ መተማመን ላይ መደረሱን አቶ ሰለሞን ጠቅሰዋል፡፡

በአራተኛው ሳምንት መድረክ ህዝብ ተወካዮች እና ፌደሬሽን ምክር ቤት አባላት ጋር በተፈጠረ የምክክር መድረክ እንደ ህዝብ እንደራሴነታቸው የሳይበር ደህንነት የሉዓላዊነት ጉዳይ መሆኑን በተመለከተ ምክክር ተደርጓል፡፡ የተቋማት አፈፃፀም ክትትልና ግምገማ በሚያደርጉበት ሂደትም የሳይበር ደህንነት አንደ አንደ መገምገሚያ ጉዳይ እንዲያደርጉት ብሎም ለሳይበር ደህንነት ዘርፉ መደላደል የሚፈጥሩ አስቻይ ፖሊሲዎችን ማርቀቅ እና ማፅደቅ ላይ የአንበሳውን ድርሻ እንዲወጡ መተማመን ላይ መደረሱን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ በማጠቃለያ መልዕክታቸው የሳይበር ደህንነት ጉዳይ የሃገር ልውና እና የሉዓላዊነት ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም ዜጋ እና ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና በቀጣይነት እንዲወጡ ዋና ዳይሬክተሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡በተለይም መገናኛ ብዙሃን የማህበረሰቡን የሳይበር ደህንነት ንቃተ ሕሊና ከመገንባት አኳያ ቀጣይነት ባለው መልኩ የሳይበር ጉዳይን እንደ አንድ የፕሮግራማቸው አካል አድርገው መውሰድና መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም ለ30 ቀናት በተካሄደው የሳይበር ደህንነት ወር በማህበረሰቡ ዘንድ ተደራሽ እንዲሆን የላቀ ሚና ለነበራቸው ሚዲያዎች፣ ተቋማት እና ድርጅቶች የላቀ ምስጋና አቶ ሰለሞን ሶካ አቅርበዋል፡፡