የደመና ማበልጸግ ፕሮጀክት ትግበራና ቀጣይ እቅዶች ላይ ምክክር ተደረገ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አገራዊ ልዩ ፕሮጀክቶች አንዱ በሆነው የደመና ማበልጸግ ትግበራ ውጤት እና ቀጣይ እቅዶች ላይ ታሕሳስ 25/2015 ዓ.ም ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተደረገ። በዚህ የምክክር መድረክ የኢመደአ ም/ዋ/ዳሬክተር አቶ ዮዳሔ አርያስላሴ አማካኝነት ውይይት ተካሂዷል።

በምክክር መድረኩ ቴክኖሎጂው ወደ አገራችን ገብቶ ወደ ትግበራ ከተገባበት 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን የተደረጉ ዋና ዋና ተግባራት፣ ስኬቶች፣ እድሎችና ተግዳሮቶች በፕሮጀክቱ ዳይሬክተር በአቶ መብራቱ ጽጌ ለባለድርሻ አካለቱ ተገልጾላቸዋል።

በመቀጠልም ከአየርና ከምድር ላይ የተደረገው የማዝነብ ኦፕሬሽን ተስፋ ሰጪ ውጤት እንዳለው የሚያሳይ ጥናት ዶ/ር ምግባር ወንዴ ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ በኦፕሬሽን ግብዓት እንዲሁም በብሔራዊ ሜትሪዎሎጂ ኢንስቲቱት መረጃ ላይ ተመስርተው የምርምር ሥራቸውን ያቀረቡ ሲሆን ከተሳታፊዎችም ጥያቄዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎበታል።

ቴክኖሎጂው በአገራችን በቅርብ እንደመጀመሩ ውጤቱን ለመገምገም ተጨማሪ ኦፕሬሽኖች፣ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች እና የጥናት ግብዓት አስፈላጊ እንደሆነ ከብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ክንፈ ኃ/ማርያም ሃሳብና አስተያየታቸውን ሰጥተውበታል።

በመጨረሻም ገለጻውን ጥናቱ ላይ በመመስረት ስለሚቀጥሉት እቅዶች፣ ትብብሮችና ተግባራት የኢመደአ ም/ዋ/ዳሬክተር በአቶ ዮዳሔ አርያስላሴ አማካኝነት ውይይት ተደርጓል። ተሳታፊዎች መርሃግብሩን አድንቀው አብሮ በመሥራትና ፕሮጀክቱን በሚጠበቅባቸው ደረጃ በሚያግዙበት ሁኔታዎች ላይ ምክክር ተደርጓል።

በወርክሾፑ የፕሮጀክቱ ባለድርሻ አካላት ከሆኑት ኢመደአ ፥ ብሔራዊ ሜቴዎሮሎጂ ኢንስቲቱት ፥ መስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ፥ ሶማሌ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ቢሮ ፥ አየርመንገድ ግሩፕ ፥ ደብሊው.አር.አይ (World Resource Institute) ፥ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሺል ኢንስቲቱት ተገኝተዋል።

በኢመደአ የዳመና ማበልጸግ ዳይሬክቶሬት ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት አንዱ ባለድርሻ አካላትን አስተባብሮ የዳመና ማበልጸግ ቴክኖሎጂን ውጤታማ እንዲሆን ኦፕሬሽን ማከናወን ነው። ይህ የደመና ማበልጸግ ፕሮጀክት በኦፕሬሽን ፣ በተግባራዊ ምርምርና ልማት፣ አስቻይ መሰረተ ልማት የማቋቋም ጉዳዮች ላይ አተኩሮ ድርቅን የመከላከል አገራዊ ተልዕኮውን የሚደግፍ ነው።

የፕሮጀክቱ ዋና ግብ ድርቅን በመቀነስ ልምላሜን በመጨመርና ምርታማነትን በማሳደግ በሰውና በእንስሳት ላይ የሚከሰትን አደጋ ማስቀረት ሲሆን በተያያዘም ቴክኖሎጂው በረዶን ለመቀነስ፣ ግድቦችን ለመሙላት፣ ለበረራ እንቅፋት የሆነውን የደመና ጭጋግ የመበተን ጥቅሞችም አሉት።