ኢመደአ ከገቢዎች ሚኒስቴር እና ከሁለት ባንኮች ጋር የሶስትዮሽ የአገልግሎት አሰጣጥ ስምምነት ተፈራረመ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የገቢዎች ሚኒስቴር ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) እና ሁለት ባንኮች ኤሌክትሮኒክስ የግብር ክፍያ ስርዓትን ለማስፋትና የግብር አከፋፈል ስርዓቱን ዘመናዊ ለማድረግ የሚያስችል የሶስትዮሽ የአገልግሎት አሰጣጥ ውል ተፈራረሙ፡፡

በስምምነት መርሀ-ግብር የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ ባደረጉት ንግግር ስምምነቱ የታክስ ስርዓቱ ለግብር ከፋዩም ሆነ ለግብር ሰብሳቢው ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንዲሁም ገቢ በትክክል እንዲሰበሰብ የሚያስችል እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ በበኩላቸው የደራሽ መተግበሪያ ፕላትፎርም የኦንላይን ክፍያዎችን ከመቆጣጠርና ከማስተዳደር ባለፈ የኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ የመተግበር ስራዎች እንደሚሰራ እና ለገቢ አሰባሰብ ስርዓት ምቹ መደላደል እንደሚፈጥር ገልፀዋል፡፡

ስምምነቱን የፈፀሙት የባንኮች ፕረዝዳንቶችም በበኩላቸው ዘመኑ ቴክኖሎጂ የግድ የሚልበትና ግብር ከፋዮችም ግብራቸውን በቀላሉ እና ቀልጣፋ በሆነ መልኩ እንዲከፍሉ አማራጭ የሚሰጥ በመሆኑ ስርዓቱ በትክክል እንዲተገበር አበክረው እንደሚሰሩ ቃልገብተዋል፡፡

በስምምነቱ የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ፣ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሰሎሞን ሶካ፣ የዘምዘም ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ሲሳይ ገብሩ እና የሄጅራ ባንክ ተጠባባቂ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳዊት ኬኖ በተገኙበት የስምምነት ፊርማው ተካሂዷል፡፡

የገቢዎች ሚንስትር የገቢ አሰራር ስርዓቱን ለማዘመን እና ለማስፋት ዘምዘም ባንክ እና ሂጅራ ባንክን ጨምሮ ከ19 ባንኮች ጋር በጋራ ለመስራት መፈራረሙ ይታወቃል፡፡