የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ ከዱባይ አለም አቀፍ ቻምበር ኦፍ ኮሜርስ የመካከለኛው ምስራቅና አፍሪካ ቀጠናዊ ማኔጀር ሚስተር ካሊድ አል አሊን ጋር ዉይይት አደረጉ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በዱባይ ኢንተርናሽናል ቻምበር ኦፍ ኮሜርስ የመካከለኛው ምስራቅና አፍሪካ ቀጠና ማኔጀር ከሆኑት ሚስተር ካሊድ አል አሊን ጋር በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል።

በምክክሩ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር የኢትዮጵያን የሳይበር ስነ-ምህዳር ደህንነት ለማስጠበቅ የቴክኖሎጂ ባለቤት መሆን ምርጫ የሌለው ጉዳይ መሆኑን በመረዳት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የተለያዩ ሀገር በቀል ቴክኖሎጂዎችን በማልማት ላይ ውጤታማ ስራ እየሰራ መሆኑን ገለጻ አድርገዉላቸዋል።

የሳይበር ደህንነት ከቴክኖሎጂ ባለቤትነት ባሻገር የሰለጠነ የሰዉ ሃይል አስፈላጊነት ከፍተኛ መሆኑን ያነሱት ዋና ዳይሬክተሩ ይህን ታሳቢ በማድረግ ተቋሙ በኢትዮ-ሳይበር ታለንት ልማት ማዕከል አማካኝነት ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ታዳጊዎችን በመቀበል ፍሬያማ ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለዉ የትብብር እና የስትራቴጂክ አጋርነት በተቋማት ደረጃም በሳይበር እና ቴክኖሎጂው ዘርፍ የተጠናከረ ስራ መሰራት እንዳለበት አቶ ሰለሞን ሶካ በውይይቱ ወቅት አንስተዋል።

በዱባይ ኢንተርናሽናል ቻምበር የመካከለኛው ምስራቅና አፍሪካ ቀጠናዊ ማኔጀር ሚስተር ካህሊድ አል አሊ በበኩላቸው አስተዳደሩ እየሰራቸው ያሉ ስራዎችን ያደነቁ ሲሆን በተለይም በታዳጊዎች ላይ ተቋሙ የሚያከናውናቸውን ተግባራት በማገዝ ረገድ በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

በዜጎቻችሁ የሚለሙ አገር በቀል የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ በመጠቀም የዲጂታል ሉዓላዊነታቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል ያሉት ማናጀሩ ከዚህ አኳያ በኢመደአ የለሙና እየለሙ የሚገኙ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የኢትዮጵያን የዲጂታል ሉዓላዊነት በማረጋገጥ ረገድ ተስፋ ሰጪ መሆኑን አንስተዋል።

ኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት እና የፈጠራ ምድር እየሆነች ነው ያሉ ሚስተር ካህሊድ አል አሊ አያይዘውም ይህም ለሌሎች ሃገራት ምሳሌ የሚሆን ስራ መሆኑን አንስተዋል።

በዱባይ ኢንተርናሽናል ቻምበር የመካከለኛው ምስራቅና አፍሪካ ቀጠናዊ ማኔጀር አቶ ካህሊድ አል አሊ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና መ/ቤትን የጎበኙ ሲሆን፡ በጉብኝታቸውም በአስተዳደሩ እየተሰሩ ያሉትን ሀገር በቀል የሳይበር ቴክኖሎጂ ውጤቶችን እና የታለንት ማዕከልን ጎብኝተዋል።