በተባበሩት አረብ ኤምሬት በተካሄደው 6ኛው ዓለማአቀፍ የዝናብ መጨመር ፎረም ላይ ኢትዮጵያ የደመና ማበልጽግ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ስላገኘችው ውጤት ለተሳታፊዎች ገለጻ ተደረገ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

በ “UAE Research Program for Rain Enhancement Science” ባዘጋጀው 6ኛው ዓለም አቀፍ የዝናብ መጨመር ፎረም ላይ የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሔ አርአያሥላሴ ኢትዮጵያ የደመና ማበልጽግ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ያገኘችውን ውጤት አስመልክተው ገለጻ አቅርበዋል።

በተባበሩት አረብ ኤምሬት በተዘጋጀው 6ኛው ዓለም አቀፍ የዝናብ መጨመር ፎረም ላይ የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሔ አርአያሥላሴ “Observation in Cloud Seeding pilot project in Ethiopia” በሚል ርዕስ ኢትዮጵያ ባለፉት ሦስት ዓመታት የደመና ማበልጽግ ቴክኖሎጂን ለመጠቀም ያደረገችውን ጥረት፣ የተገኙ ውጤት እና ቀጣይ እቅዶችን ከተለያዩ አገራት ለተገኙ የፎረሙ ተሳታፊዎች ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አቶ ዮዳሄ እንዳሉት ፕሮጀክቱ በሀገራችን ዝናብ አጠር በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ አርብቶ አደሮችን እና አርሶ አደሮችን ህይወት ከመቀየር ባለፈ አገራችን የተያያዘችውን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታን ከማገዝ አንፃር የራሱ የሆነ ትልቅ ፋይዳ ያለው ነው ብለዋል፡፡

የደመና ማበልፀግ ፕሮጅክት በኢትዮጵያ የተጀመረው እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር 2021 በክብር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አነሳሽነት በተባበሩት አረብ ኤምሬት(UAE) በተደረገ ቴክኒካል ድጋፍ መሆኑን ም/ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ዮዳሔ ለፎረሙ ለተሳታፊዎች ተናግረዋል።