የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ዑማር ጌሌ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኙ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

 

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2014 የጂቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ዑማር ጌሌ ከኢፌደሪ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጋር በመሆን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና መስሪያ ቤትን ጎብኝተዋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛውና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ለልዑክ ቡድኑ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እየሰራቸው ያሉ ስራዎችን በተመለከተ በለተይም ደግሞ በደመና ማልማት (cloud seeding) ፣ በሰው አልባ አውሮፕላን ምርምርና ልማት ፣በሳይበር ደህንነት እንዲሁም ደህነንታቸውን የጠበቁ የኮሚዩኒኬሽን ፕላትፎርሞች ምርምርና ልማት ዙሪያ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለፕሬዚዳንቱ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ዑማር ጌሌ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በሳይበር ደህንነት እና ተያያዥ ዘርፎች እየሰራ ያለውን ስራ አድንቀዋል፡፡

የጂቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ዑማር ጌሌ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ትናንት አዲስ አበባ መግባታቸውን ይታወሳል።