የሳይበር ደህንነት አደረጃጀት እና የሥራ መደብ ማዕቀፍ ተቋማት የሳይበር ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ አስቻይ ነው - ኢመደአ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]አዲስ አበባ፡ ሐምሌ 18/2014 ዓ/ም፡ ተቋማት ለሳይበር ጥቃት ተጋላጭ ከሚያደርጓቸው ክፍተቶች መካከል በዋናነት ያላቸውን መረጃ እና የመረጃ መሰረተ ልማቶች ለማስተዳደርና ለመምራት የሚያስችል የሳይበር ደህንነት አደረጃጀት እንደየተቋሞቻቸው ዓውድና ነባራዊ ሁኔታ ተግባራዊ አለማድረጋቸው ነው፡፡ በመሆኑም የተቋማትን መረጃዎች፣ የመረጃ መሰረተ ልማቶችንና ስርዓቶችን ስጋት፣ተጋላጭነት እና ጥቃትን ለመከላከል የሳይበር አደረጃጀትና አስተዳደር መፍጠር አስፈላጊ እንደሆነ እሙን ነው፡፡

ከዚህ አኳያ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 808/2006 አንቀፅ 6 ንዑስ አንቀፅ 2 እና 3 መሰረት ተቋማዊ "የሳይበር ደህንነት አደረጃጀት እና የሥራ መደብ ማዕቀፍ" ለመንግስት ተቋማት እና ለቁልፍ የግል ተቋማት እንደየአውዳቸው የሚተገብሩት ሰነድ አዘጋጅቷል፡፡

በኢመደአ የተዘጋጀው "የሳይበር ደህንነት አደረጃጀት እና የስራ መደብ ማዕቀፍ" ዋና ዓላማ በተቋማት ደረጃ የሳይበር ደህንነት የስራ ድርሻና ኃላፊነትን ለይቶ ለማስቀመጥ፤ የተቋማትን መረጃዎች፣ የመረጃ መሰረተ ልማቶችና የመረጃ ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥርዓት እንዲኖር ለማስቻል ብሎም ከሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ ስታንዳርዶች እና ህጎች ጋር የተጣጣመ አደረጃጀት በተለያዩ ተቋማት እንዲኖር ማድረግ ነው፡፡ ማዕቀፉ በመርህ ደረጃ ተጠያቂነት፣ ኃላፊነት፣ አውዳዊነት እና ቅንጅትና አጋርነትን መሰረት ያደረገ ሲሆን ተቋማት እንደየአውዳቸውና ተልኳቸው መርሆቹን ማስፋት ይችላሉ፡፡

ማዕቀፉ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ እንደሚሆን የሚጠበቅ ሲሆን ተቋማት እንደየራሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ እና ዓውድ ተግባራዊ የሚያደርጉት ነው፡፡

ይህ ሰነድ ተቋማት የሳይበር ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ የሳይበር ደህንነት የስራ ክፍልን በምን አይነት ሁኔታ እና ደረጃ ማዋቀር እንዳለባቸው በውስጡም በመሰረታዊነት ሊይዛቸው የሚገቡ ንዑስ የስራ ክፍሎችን እንዲሁም የሳይበር ደህንነት ባለሞያዎቻቸው ምን አይት አቅም ሊኖራቸው እንደሚገባ በዝርዝር ያመላከተ ነው፡፡

ኢመደአ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ይህንን የሳይበር ደህንነት አደረጃጀት እና የሥራ መደብ ማዕቀፍ ያዘጋጀ ሲሆን፤ ተቋማት ይህንን አደረጃጀት እንዲተገብሩ ለማስቻል ሙያዊ ድጋፍ እና የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት፣ እንዲሁም የተቋማትን አውድ ባገናዘበ ሁኔታ በየጊዜው ተፈጻሚነቱን ክትትል የሚያደርግ ይሆናል፡፡

በኢመደአ የተዘጋጀውን የሳይበር ደህንነት አደረጃጀት እና የሥራ መደብ ማዕቀፍ ሙሉ ሰነድ ለማግኘት ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ፡፡