የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሀሚድ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር / ትዕግስት ሀሚድ ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የክርስትና እምነት ተከታዮች የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሯ በእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸዉ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓት የሚከበረው የትንሳኤ በዓል ለሀገራችን እና ለህዝቦቿ የሠላም፣ የፍቅርና የደስታ በዓል እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

 የዘንድሮውን የትንሳኤ በዓል ስናከብር ኢትዮጵያዊያን ከምንታወቅባቸው ድንቅ እሴቶቻችን መሀል የመደጋገፍ በተለይም በፈተና እና በችግር ወቅት የመረዳዳት ባህላችን በተግባር የምናሳይበት ሊሆን እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

በዓሉን ስናከብር በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ከቤት ንብረታቸው እና ከቄያቸው ተፈናቀለው ለሚገኙ ወገኖቻችን አስፈላጊውን ስነ ልቦናዊ፣ ብሎም ቁሳዊ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ቀጣይነት ባለው መልኩ የማገዝ ሊሆን እንደሚገባ ያነሱት / ትዕግስት  ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን ያለንን በማካፈል ለወገን አለኝታነታችንን የምናሳይበት መሆን እንደሚገባዉ ገልጸዋል፡፡

የበዓላት ወቅት ከሌሎች ጊዜያት በተለየ ማህበረሰባችን በከፍተኛ ደረጃ ግብይት የሚፈጽሙበት፤ በተለይም ደግሞ የሚፈጸመው ግብይት በአብዛኛው በሞባይል ባንኪንግና በበይነ መረብ አማካኝነት መሆኑና ሰፊ የመልዕክት ልዉዉጦች መኖራቸዉን ተከትሎ የዲጂታል ማጭበርበሮች ስለሚጨምሩ ማህበረሰባችን ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ ሊደርሱ ከሚችሉ የገንዘብ ማጭበርበሮች (fraud) እንዲጠነቀቁ / ትዕግስት ሃሚድ አሳስበዋል።

                       መልካም የትንሳኤ በአል!

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች