ለኦሮሚያ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ባለስልጣን የሳይበር ደህንነት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ለኦሮሚያ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች የሳይበር ደህንነት የግንዛቤ ማስጨበጫ የግማሽ ቀን ስልጠና ሰጠ፡፡

ስልጠናዉ በዋናነት ትኩረት ያደረገው በሳይበር ምህዳር ምንነት እና  ባህሪያት፣ ምህዳሩ የፈጠራቸው መልካም አጋጣሚዎችና ተግዳሮቶች የሳይበር ጥቃት  የሚያስከትለው  ኢኮኖሚያዊ፣ ፓለቲካዊ እና ሁለን አቀፍ ተጽዕኖዎች፣ የሳይበር ደህንነት መርሆዎች እንዲሁም  የሳይበር ጥቃትን ለመከላከል የሚያስችሉ   ሁሉን አቀፍ የሳይበር የመከላከያ መንገዶች  ናቸው፡፡

የኦሮሚያ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ባለስልጣን ከፍተኛ የመረጃ ሀብት የያዘ ግዙፍ ተቋም እንደመሆኑ ይህንኑ  ግዙፍ የመረጃ ሀብት ደህንነት ለማረጋገጥ የሚመጥን ሁሉን አቀፍ የሳይበር ደህንነት  ስርዓት አንዲኖር በማስፈለጉ  ስልጠናው እንደተዘጋጀ  የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር  አቶ መኮንን በየነ ገልጸዋል፡፡

የሳይበር ደህንነት የማረጋገጥ ጉዳይ በከፍተኛ አመራሩ ላይ ብቻ የሚወሰን ባለመሆኑ ሁሉንም ሰራተኞች ባማከለ መልኩ በቀጣይ መሰል ስልጠናዎች  እንደሚዘጋጁ ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

የሳይበር ደህንነት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ለአንድ ጊዜ ተሰጥቶ የሚተው ሳይሆን ቀጣይነት ባለው መልኩ በየጊዜው ሊደረግ የሚገባዉ ጉዳይ መሆኑን  የኢመደአ የሳይበር ደህንነት ባህል ግንበታ ዲቪዢን ሃላፊ አቶ ቢንያም ማስረሻ ገልጸዋል። የኦሮሚያ የሳይንስ አና ቴክኖሎጂ ባለስልጣን ተቋማዊ የሳይበር ደህንነቱን ለማረጋገጥ ያሳየው ቁርጠኝነት ሊደነቅ የሚገባው እና ለሌሎች ክልሎችም  አርአያ ሊሆን የሚችል ተግባር መሆኑን  አቶ ቢኒያም ተናግረዋል፡፡

በሀገራችን የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች ማደግ እና የተጠቃሚዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመር ጋር ተያይዞ ተቋማትም ሆኑ ግለሰቦች የሚሰሯቸው ስራዎች በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ የሳይበር ምህዳሩን  መሰረት ያደረጉ ናቸው፡፡

በመሆኑም  ተቋማት የሳይበር ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠታቸው የምርጫ ብቻ ሳይሆን የሕልውና ጉዳይም እየሆነ መምጣቱን በስልጠናው ወቅት ተጠቅሷል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች