ኢመደአ በቀጨኔ ሴት ሕጻናት ጊዜያዊ ማቆያና ማቋቋሚያ ማዕከል ለሚገኙ ታዳጊና ወጣት ሴቶች የማዕድ ማጋራት እና የትምህርት ቁሳቁስ መግዣ ድጋፍ አደረገ

Nested Applications

Asset Publisher

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ አመራሮች የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኙ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ አመራሮች የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኙ Fri, 24 Nov 2023

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የሸገር ከተማ አስተዳደር የሥራ ውል ስምምነት ተፈራረሙ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የሸገር ከተማ አስተዳደር የሥራ ውል ስምምነት ተፈራረሙ Mon, 27 Nov 2023

ኢትዮጵያ በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ከሀገራት ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኗ ተገለጸ

ኢትዮጵያ በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ከሀገራት ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኗ ተገለጸ Fri, 17 Nov 2023

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በኢትዮጵያ የማልታ ኤምባሲ ጋር በመተባበር በሳይበር ዲፕሎማሲ ዙሪያ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በኢትዮጵያ የማልታ ኤምባሲ ጋር በመተባበር በሳይበር ዲፕሎማሲ ዙሪያ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ Mon, 27 Nov 2023

Asset Publisher

null ኢመደአ በቀጨኔ ሴት ሕጻናት ጊዜያዊ ማቆያና ማቋቋሚያ ማዕከል ለሚገኙ ታዳጊና ወጣት ሴቶች የማዕድ ማጋራት እና የትምህርት ቁሳቁስ መግዣ ድጋፍ አደረገ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) የ2016 አዲስ አመት መቀበያን እና የትውልድ ቀንን ምክንያት በማድረግ በቀጨኔ የሴት ሕጻናት ጊዜያዊ ማቆያና ማቋቋሚያ ማዕከል ውስጥ ለሚገኙ 104 (አንድ መቶ አራት) ለሚሆኑ ታዳጊና ወጣት ሴቶች የምሳ ግብዣ፣ የትምህርት ቁሳቁስ መግዣ፣ እና ለማዕከሉ የሚያስፈልጉ የተለያዩ የቢሮና የጽዳት ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ፡፡

በአስተዳደሩ ዋና መ/ቤት በተደረገው የምሳ ግብዣ እና የትምህርት ቁሳቁስ መግዣ ድጋፍ ላይ የተገኙት የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት ባስተላለፉት መልዕከት በቀጨኔ የሴት ሕጻናት ጊዜያዊ ማቆያና ማቋቋሚያ ማዕከል ውስጥ የሚገኙ ታዳጊና ወጣት ሴቶች መጪውን 2016 አዲስ አመት በብሩህ ተስፋና በደስታ እንዲቀበሉት በማሰብ የምሳ ግብዣ እና የትምህርት ቁሳቁስ መግዣ ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ የተደረገው ድጋፍ በዋናነት ኢመደአ በማዕከሉ ውስጥ ለሚገኙ ታዳጊና ወጣት ሴቶች ያለውን አጋርነት ለማሳየት መሆኑን የገለጹት ወ/ሮ አስቴር ሌሎች ተቋማትና ግለሰቦችም ይህንን በጎ ተግባር ሊቀጥሉበት ይገባል ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በሕጻናት ማቆያ ማዕከሉ የሚገኙ ታዳጊ ወጣት ሴቶች የነገ ሃገር ተረካቢ ዜጎች እንዲሆኑ ጠንክረው መስራት እንዳለባቸውም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የቀጨኔ የሴት ሕጻናት ጊዜያዊ ማቆያና ማቋቋሚያ ማዕከል ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ጥሩወርቅ ደበበ ባስተላለፉት መልዕክት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ላደረገላቸው ድጋፍ አምስግነው፤ ኢመደአ የአገሪቱን የሳይበር ደህንነት ከማስጠበቅ ባሻገር ማህበራዊ ሃላፊነቱ በትክክል የሚወጣ ሕዝባዊ ተቋም እንደሆነ የሚያረጋግጥ በጎ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው የሕይወት ልምዳቸውን ያካፈሉት ዶ/ር ደረጄ ባስተላለፉት መልዕክት “ከወላጅ አልባ ሕጻናት ማሳደጊያ ማዕከል በመነሳት ትልቅ ደረጃ መድረስ እንደሚቻል የእኔ ሕይወት ሕያው ምስክር ነው” ብለዋል፡፡ በመሆኑም ታዳጊ ወጣት ሴቶች አሁን ያሉበትን ደረጃና ሕይወት ሳይሆን የነገ ሕልማቸውን ታሳቢ በማድረግ ጠንክረው እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡

በሌላም በኩል “የሸጋ ትውልድ ማሕበር” ሥራ አስኪያጅ አቶ ሳሙኤል ገረመው በማዕድ ማጋራትና የድጋፍ መርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ባስተላለፉት መልዕክት በማዕከሉ ውስጥ የሚገኙ ታዳጊና ወጣት ሴቶች ያላቸውን እምቅ አቅምና ልዩ ተሰጥኦ እንዲያወጡና ለትውልድ የሚተርፍ ሥራ እንዲሰሩ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍና ስልጠና እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ በኢመደአ የኢትዮ ሳይበር ታለንት ልማት ማዕከል የሚገኙ ባለ ልዩ ተሰጥኦ ታዳጊ ወጣቶች በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ለታዳጊና ወጣት ሴቶቹ ልምዳቸውንና ተሞክሯቸውን አካፍለዋል፡