የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የሚዲያ ጉዳዮች ሃላፊ ታላል አል አዘሪ ጋር ተወያዩ - INSA

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የሚዲያ ጉዳዮች ሃላፊ ታላል አል አዘሪ ጋር ተወያዩ

Nested Applications

Asset Publisher

የስማርት ከተማን ለመገንባት በሚከናወኑ ተግባራት የሳይበር ደህንነትን ማረጋገጥ ይገባል - ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ፡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር

የስማርት ከተማን ለመገንባት በሚከናወኑ ተግባራት የሳይበር ደህንነትን ማረጋገጥ ይገባል - ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ፡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር Mon, 16 Dec 2024

“የኤርፖርት እና ድንበር አስተዳደር ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም” የትብብር ስምምነት ተፈረመ

“የኤርፖርት እና ድንበር አስተዳደር ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም” የትብብር ስምምነት ተፈረመ Mon, 16 Dec 2024

ኢመደአ የፀረ ጾታዊ ጥቃት ፣ የአካል ጉዳተኞች፣ የጸረ-ኤድስ እና የአፍሪካ ወጣቶች ቀንን አክብሮ ዋለ

ኢመደአ የፀረ ጾታዊ ጥቃት ፣ የአካል ጉዳተኞች፣ የጸረ-ኤድስ እና የአፍሪካ ወጣቶች ቀንን አክብሮ ዋለ Mon, 16 Dec 2024

የጋራ ሀገርን ለመገንባት የጋራ ትርክት መገንባትና የጋራ መግባባት መፍጠር እንደሚገባ ተገለጸ

የጋራ ሀገርን ለመገንባት የጋራ ትርክት መገንባትና የጋራ መግባባት መፍጠር እንደሚገባ ተገለጸ Fri, 6 Dec 2024

Asset Publisher

null የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የሚዲያ ጉዳዮች ሃላፊ ታላል አል አዘሪ ጋር ተወያዩ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የሚዲያ ጉዳዮች ሃላፊ ከሆኑት ታላል አል አዘሪ ጋር በሳይበር ደህንነት እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡

በዉይይቱም የሳይበር ቴክኖሎጂ ባለቤትነትን በማረጋገጥና በዘርፉ ያለዉን የሰዉ ሃይል እጥረት በመቅረፍ ረገድ በጋራና በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

ኢመደአ የኢትዮጵያን የሳይበር የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን ለማረጋገጥ እየሰራ ያለዉ ስራ ለሌሎች አፍሪካ አገራት ምሳሌ ሊሆን የሚችል መሆናቸዉን የጠቀሱት ታላል አል አዘሪ ይህ መልካም ተሞክሮ ወደ ሌሎች አፍሪካ አገራት መስፋት የሚገባዉ መሆኑን ገልጸዋል። አያይዘውም በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ከኢመደአ ጋር በሳይበር ደህንነት ዘርፍ በይበልጥ በታዳጊዎች የሳይበር ታለንት ልማት ላይ በትብብር መስራት ፍላጎት እንዳለዉ ሚስተር ታላል ገልጸዋል።

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በበኩላቸው ኢመደአ በሳይበር ቴክኖሎጂ ባለቤትነት እንዲሁም በሳይበር ታለንት ልማት ያካበተውን ተሞክሮ ለሌሎች የአፍሪካ ሐገራት ለማካፈል ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ሰለሞን ሶካ ከታላል አል አዘሪ ጋር ካደረጉት ውውይት ባሻገር ኢመደአ ሐገራዊ የቴክኖሎጂ እና የእውቀት ባለቤትነትን በማረጋገጥ ረገድ እየሰራቸው የሚገኙ ሥራዎችን፤ የኢትዮ ሳይበር ታለንት ልማት ማዕከልን፤ እና ሌሎች ተቋማዊ ምርትና አገልግሎቶችን አስጎብኝተዋቸዋል፡፡