አስተዳደሩ ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ የስራ አመራር አባላት በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ

Nested Applications

Asset Publisher

ባለፉት 9 ወራት 453 የተከለከሉ የመረጃ እና የመገናኛ ቴክኖሎጂ እቃዎች ወደ ሀገር እንዳይገቡ ፍቃድ ተከልክሏል

ባለፉት 9 ወራት 453 የተከለከሉ የመረጃ እና የመገናኛ ቴክኖሎጂ እቃዎች ወደ ሀገር እንዳይገቡ ፍቃድ ተከልክሏል Fri, 12 May 2023

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከሜታ/ፌስቡክ ድርጅት ጋር በመተባበር ለኮሚዩኒኬሽን ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከሜታ/ፌስቡክ ድርጅት ጋር በመተባበር ለኮሚዩኒኬሽን ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ Tue, 9 May 2023

ባለፉት 9 ወራት የሳይበር ጥቃቶችን በመከላከል ከ19 ቢሊዮን ብር በላይ ማዳን ተቻለ

ባለፉት 9 ወራት የሳይበር ጥቃቶችን በመከላከል ከ19 ቢሊዮን ብር በላይ ማዳን ተቻለ Thu, 4 May 2023

የኢትዮ ሳይበር ታለንት ልማት ማዕከል በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ብቁ የሰው ሀይል ለማፍራት እየሰራ መሆኑ ተገለጸ

የኢትዮ ሳይበር ታለንት ልማት ማዕከል በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ብቁ የሰው ሀይል ለማፍራት እየሰራ መሆኑ ተገለጸ Wed, 3 May 2023

Asset Publisher

null አስተዳደሩ ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ የስራ አመራር አባላት በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ

 

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 16 ፣ 2014 የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ የስራ አመራር አባላት በሳይበር ደህንነት ዙሪያ የግማሽ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

በስልጠናው መርሀ ግበር ላይ የተገኙት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሳይበር ደህንነት ጉዳይ ትኩረት ባለመሰጠቱ በርካታ ጉዳቶች እየደረሱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሳይበር ደህንነትን ለማረጋገጥ ሶስት መሰረታዊ ነገሮችን ማሟላት ይጠይቃል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ፤እነዚህም እውቀትና ክህሎት ያለው የሰው ሃይል፣የዘመኑ ቴክኖሎጂዎችና ትክክለኛ የአሰራር ስርዓት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ይህ ሲሟላም የሳይበር ደህንነት አስተማማኝ ደረጃ ደርሷል ማለት እንደሚቻል ዶ/ር ሹመቴ ገልፀዋል፡፡

በቀጣይም አስተዳደሩ ተመሳሳይ ስልጠና ለባንኩ አመራሮችና ሰራተኞች ለመስጠት ፈቃደኛ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚደንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው በበኩላቸው የኢንፎርሜሽን ዲጂታል ስርዓት የሀገራት መወዳደሪያ ጡንቻ በሆነበት በዚህ ወሳኝ ወቅት የተቋማት መረጃን ከማንኛውም አይነት የሳይበር ጥቃት መጠበቅ ትኩረት የሚሻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሀገራት ሉአላዊነታቸውንና አጠቃላይ ህልውናቸውን አረጋግጠው ለመኖር የዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅምን መገንባት አማራጭ ሳይሆን ግዴታ የሆነበት ዘመን ላይ እንገኛለን ያሉት የባንኩ ፕሬዝደንት፤ከዚህ አንጻር የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ስልጠናውን ለመስጠት ላሳየው ተነሳሽነት ምስጋናቸውንም አቅርበዋል፡፡