አስተዳደሩ ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ የስራ አመራር አባላት በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ

Nested Applications

Asset Publisher

የቁልፍ መሰረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነትን መጠበቅ የሀገር ደኅንነትና ሉዓላዊነትን መጠበቅ ነው

የቁልፍ መሰረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነትን መጠበቅ የሀገር ደኅንነትና ሉዓላዊነትን መጠበቅ ነው Sun, 13 Oct 2024

“የቁልፍ መሰረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት በኢትዮጵያ” በሚል ርእስ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀረበ

“የቁልፍ መሰረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት በኢትዮጵያ” በሚል ርእስ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀረበ Sun, 13 Oct 2024

የቁልፍ መሰረተ ልማቶችን የሳይበር ደህንነት ማስጠበቅ የሁሉም ተቋማትና ዜጎች ኃላፊነት ነው

የቁልፍ መሰረተ ልማቶችን የሳይበር ደህንነት ማስጠበቅ የሁሉም ተቋማትና ዜጎች ኃላፊነት ነው Sun, 13 Oct 2024

ባለንበት የዲጂታል ዘመን ሀገራዊ ሉዓላዊነታችንን ለማረጋገጥ የቁልፍ መሰረተ ልማቶቻችንን የሳይበር ደህንነት መጠበቅ ወሳኝ ጉዳይ ነው

ባለንበት የዲጂታል ዘመን ሀገራዊ ሉዓላዊነታችንን ለማረጋገጥ የቁልፍ መሰረተ ልማቶቻችንን የሳይበር ደህንነት መጠበቅ ወሳኝ ጉዳይ ነው Sun, 13 Oct 2024

Asset Publisher

null አስተዳደሩ ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ የስራ አመራር አባላት በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ

 

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 16 ፣ 2014 የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ የስራ አመራር አባላት በሳይበር ደህንነት ዙሪያ የግማሽ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

በስልጠናው መርሀ ግበር ላይ የተገኙት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሳይበር ደህንነት ጉዳይ ትኩረት ባለመሰጠቱ በርካታ ጉዳቶች እየደረሱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሳይበር ደህንነትን ለማረጋገጥ ሶስት መሰረታዊ ነገሮችን ማሟላት ይጠይቃል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ፤እነዚህም እውቀትና ክህሎት ያለው የሰው ሃይል፣የዘመኑ ቴክኖሎጂዎችና ትክክለኛ የአሰራር ስርዓት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ይህ ሲሟላም የሳይበር ደህንነት አስተማማኝ ደረጃ ደርሷል ማለት እንደሚቻል ዶ/ር ሹመቴ ገልፀዋል፡፡

በቀጣይም አስተዳደሩ ተመሳሳይ ስልጠና ለባንኩ አመራሮችና ሰራተኞች ለመስጠት ፈቃደኛ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚደንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው በበኩላቸው የኢንፎርሜሽን ዲጂታል ስርዓት የሀገራት መወዳደሪያ ጡንቻ በሆነበት በዚህ ወሳኝ ወቅት የተቋማት መረጃን ከማንኛውም አይነት የሳይበር ጥቃት መጠበቅ ትኩረት የሚሻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሀገራት ሉአላዊነታቸውንና አጠቃላይ ህልውናቸውን አረጋግጠው ለመኖር የዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅምን መገንባት አማራጭ ሳይሆን ግዴታ የሆነበት ዘመን ላይ እንገኛለን ያሉት የባንኩ ፕሬዝደንት፤ከዚህ አንጻር የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ስልጠናውን ለመስጠት ላሳየው ተነሳሽነት ምስጋናቸውንም አቅርበዋል፡፡