ለአማራ ባንክ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በሳይበር ደህንነት ንቃተ ህሊና ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ለአማራ ባንክ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በሳይበር ደህንነት ንቃተ ህሊና ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና አማራ ባንክ የተቀናጀ የሳይበር ደህንነት መፍትሄ ፕሮጀክት ላይ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመው በሳይበር ደህንነት ዙሪያ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡

በዛሬው እለት የዚሁ ፕሮጀክት አካል የሆነው የሳይበር ደህንነት ንቃተ ህሊና ወርክሾፕ የአማራ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ሄኖክ ከበደ እና ከፍተኛ የባንኩ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

የአማራ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ሄኖክ ከበደ በስልጠናው ላይ ባስተላለፉት መልእክት በወቅታዊነት በዓለም ላይ ከሚስተዋለው የሳይበር ደህንነት ስጋትና ተጋላጭነት አንጻር ዓለም የደረሰበትን ቴክኖሎጂ ለማወቅና ለመጠቀም፣ የህግ ማዕቀፎችና የቁጥጥር ስርዓቶች ለመዘርጋት፣ ንቃተ ህሊናን ለማሳደግ፤ እንዲሁም ወቅታዊና ታሳቢ የሳይበር ደህንነት ስጋቶችን ከግምት ያስገባ የፖሊሲ አቅጣጫዎችንና ስትራቴጂዎችን መንደፍ እና የክትትልና ግምገማ ሥርዓት መዘርጋት በተለይ ለፋይናንስ ተቋማት አስፈላጊ መሆኑን ከኢመደአ ጋር ፕሮጀክት ቀርፀን በጋራ እየሰራን የምንገኝ ሲሆን ይኸው የአንድ ሰሞን ስራ ሳይሆን ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የኢመደአ የሳይበር አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀኒባል ለማ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት አለማቀፍ የሳይበር ትንኮሳዎች እና ስጋቶችን በተመለከተ በተለይ የፋይናንስ ተቋማት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው ጠቁመዋል፡፡ አያይዘውም የፋይናንስ ተቋማት የሳይበር ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ በዋናነት ከቴክኖሎጂ፣ ከአሰራር ስርአት እና ከሰው ሃይል አኳያ እራሳቸውን በየጊዜ መፈተሽና ክፍትተ ባለባቸው ቦታዎች ቀጣይነት ያለው መፍትሄ መስጠት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከአማራ ባንክ ጋር እየሰራ የሚገኘው ፕሮጀክት አሁን ያለበት ደረጃ፣ እስከአሁን የተሰሩ ስራዎችና እንዴት እየተሰራ እንዳለ እና በሳይበር ደህንነት ንቃተ ህሊና ዙሪያ ለባንኩ ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ተሰጥቶ ፕሮግራሙ ተጠቃሏል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች