የታንዛኒያ ከፍተኛ የመከላከያ ሃላፊዎች የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኙ
Nested Applications
Asset Publisher
የታንዛንያ ከፍተኛ የመከላከያ ሃላፊዎች በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በመገኝት ጉብኝት አደረጉ።
በጉብኝቱ የተቋሙን የታለንት ልማት ማዕከልን ጨምሮ በራስ አቅም የለሙ የመረጃና ኮሚዩኒኬሽንና፤ እንዲሁም ሌሎች አስቻይ የቴክኖሎጂ ምርትና አገልግሎቶችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ ወቅት የተገኙት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ አጠቃላይ ተቋሙ በመንግስትና በህዝብ የተጣለበትን ሃላፊነት በሚገባዉ ልክ ለመወጣት በራሱ አቅም እያለማቸዉ ስላሉ ምርትና አገልግሎቶች ገለጻ አድርገዋል።