ተለዋዋጭ፣ ኢ-ተገማች፣ ውስብስብና አሻሚ በሆነዉ ዓለም ዉስጥ ነገን አልሞ መስራት እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ መሆኑን የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ገለጹ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ተለዋዋጭ፣ ኢ-ተገማች፣ ውስብስብና አሻሚ በሆነዉ ዓለም ስርዓት ዉስጥ ነገን አልሞ መስራት እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ገለጹ።

ይህን ያሉት “Future foresight and planning in the Volatile, Uncertain, Complex and Ambiguous (VUCA) world” በሚል ርዕስ የኢመደአ ከፍተኛና መካከለኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት የዉይይት መድረክ ላይ ነዉ።

የዉይይት መነሻ ጽሁፍ በአቶ ሃፍቱ ግርማይ የቀረበ ሲሆን በቩካ (VUCA) የአለም ነባራዊ ሁኔታ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት እንደ ተቋምና እንደ ሀገር ምን መደረግ አለበት በሚሉ ጉዳዮች ላይ ዘርዘር ያሉ ሃሳቦችን አቅርበዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (የኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በተለዋዋጭ፣ ኢ-ተገማች፣ ውስብስብና አሻሚ በሆነዉ ዓለም ዉስጥ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት እንደ ተቋምና እንደ ሀገር አርቆ ማሰብ እና ነገን አልሞ መስራት እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ለዚህ ደግሞ ወደ ውስጥ መመልከትና ምን አለን የሚለውን አውቆ፣ ሀብትን ለይቶና አሰባስቦ፣ ቅድሚያ ለሚገባው ጉዳይ ቅድሚያ ሰጥቶ፤ የጋራ ዓላማና ርዕይ ይዞ መስራት ተገቢ ነው ብለዋል፡፡

በዚህ ረገድ ኢመደአ የመደመር መንገድን ተከትሎ የራስን ሀገር በቀል ፍልስፍና በመጠቀም ነገን ዛሬ አልሞ በነገው ዓለም ስኬታማ ለመሆን ዛሬ ላይ መስራት የሚገባውን እየሰራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

ኢመደአ መጻኢ የዓለም የቴክኖሎጂ ለዉጦችን የሚያጠና ክፍል አቋቁሞ እየሰራ መሆኑን ያወሱት ወ/ሮ ትዕግስት የወደፊት ስጋቶችን ታሳቢ ያደረገ የሳይበር ደህንነት ዝግጁነት መፍጠር እንደሚገባም ማጠቃለያ ንግግራቸዉ አሳስበዋል።

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች