ከሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የተውጣጡ የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች ኢመደአን ጎበኙ
ከሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የተውጣጡ የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች ኢመደአን ጎበኙ
ከኢፌዲሪ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የተውጣጡ የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ጎበኙ፡፡
በኢፌዲሪ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ስር የሚገኘው የሳይበር ዋና ዳይሬክቶሬት ከሚኒስቴሩ የተለያዩ ክፍሎች የተውጣጡ የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎችን በመሰረታዊ የሳይበር ደህንነት ዙሪያ እያሰለጠነ የሚገኝ ሲሆን፤ ሰልጣኞቹ በኢመደአ ተገኝተው ሀገራዊ የሳይበር ደህንነትና ሉኢዓላዊነት የማስጠበቅ ሥራ ምን እንደሚመስል ለመመልከት ችለዋል፡፡
በተለይም ሀገራዊ የሳይበር ደህንነትን ከማረጋገጥ አኳያ በአስተዳደሩ የለሙ ምርትና አገልግሎቶችን ለመመልከት ችለዋል፡፡
በጉብኝቱ የተገኙት የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተር እና የኢንፎርሜሽን አሹራንስ ዘርፍ ሃላፊ ተወካይ አቶ ሃኒባል ለማ ለጎብኚዎቹ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በመልዕክታቸውም ኢመደአ የሀገሪቱን ዲጂታል ሉዓላዊነት ለመጠበቅና በምርምርና ልማት ላይ የተመሰረተ የቴክኖሎጂና የእውቀት ባለቤትነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ሀገራዊ የሳይበር ደህንነትን የማረጋገጥ ጉዳይ በአንድ ተቋም የተናጠል ጥረት ብቻ እንደማይረጋገጥ የገለጹት አቶ ሃኒባል፤ ሁሉም ተቋማት እና ዜጎች የሳይበር ደህንነትን በማረጋገጥ ረገድ የየራሳቸውን ሚናና ሃላፊነት መወጣት እንደሚጠበቅባቸውም ተናግረዋል፡፡